የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንዲቋቋም ወሰነ
ብልጽግና ፓርቲ አካታችና ሁሉን አቀፍ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን አምኖ መቀበሉን ማስታወቁ ይታወሳል
ምክር ቤቱ ውሳኔው ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንዲቋቋም ወሰነ፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ አርብ ታህሳስ 1/2014 ዓ/ም ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ በቀረበለት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
በቅርቡ ሁሉን አካታች የሆነ ብሄራዊ የምክክር መድረክ ማካሄድ እንደሚጀመር ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ
መንግስት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ይሁኝታ አግኝቶ ሲመረጥ ቃል ከገባባቸው አገራዊ ጉዳዮች መካከል ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አንዱ መሆኑንም ምክር ቤቱ አስታውሷል፡፡
“እንደ አማራ ክልል አስቸኳይ ምክክርም ንግግርም እንፈልጋለን”- አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር
መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ ምልዓተ ህዝቡ ተቀራራቢና በአገራዊ አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ አካታች አገራዊ ምክክሩን ተግባራዊ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለውሳኔ እንደቀረበለትም ነው ምክር ቤቱ ያስታወቀው፡፡
በረቂቅ አዋጁ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑንም ምክር ቤቱ ገልጿል።
ብሔራዊ የምክክር መድረክ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር ማይንድ ኢትዮጵያ አስታወቀ
የተጀመረውን ሃገራዊ የፖለቲካ ሽግግር ሂደት ስለሚጠናከርበት ሁኔታ ትናንት ሃሙስ የመከረው መሪው ብልጽግና ፓርቲ አካታችና ሁሉን አቀፍ ምክክር ከለውጡ መነሻ ጀምሮ ሲቀነቀን የነበረ ሐሳብ መሆኑን በማስታወስ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን አምኖ መቀበሉን ማስታወቁ ይታወሳል።
ሀገራዊ ምክክሩም ሀገር በቀል የሆነ፣ በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያግዝ፣ ከሕዝቡ ባህልና ዕሴት ጋር የሚጣጣም፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በዘላቂነት ለማስከበር የሚረዳ መሆን እንዳለበት አጽንዖት መሰጠቱንም የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ መግለጻቸው አይዘነጋም።