የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች የተመድ ሰራተኞችን አሰሩ
ሁለት ሴት እና ዘጠኝ ወንድ የሆኑት ሰራተኞች በየመን በሚገኙ አምስት የተለያዩ የተመድ ኤጀንሲዎች እና በየመን ለተመድ ልዩ መልእክተኛ ሲሰሩ ነበር
የተመድ ቃል አቀባይ ተመድ በየመን ያሉት የተመድ ሰራተኞች እስር እጅጉን እንዳሳሰበው እና ለምን እንደታሰሩ ከሀውቲዎች ማብራሪያ እየፈለገ ነው ብለዋል
የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች የተመድ ሰራተኞችን አሰሩ።
የሀውቲ ታጣቂዎች ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ 11 የተመድ ሰራተኞች ማሰራቸውን እና ተመድ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንደሚፈልግ የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ ተመድ በየመን ያሉት የተመድ ሰራተኞች እስር እጅጉን እንዳሳሰበው እና ለምን እንደታሰሩ ከሀውቲዎች ማብራሪያ እየፈለገ ነው ብለዋል።
ሁለት ሴት እና ዘጠኝ ወንድ የሆኑት ሰራተኞች በየመን በሚገኙ አምስት የተለያዩ የተመድ ኤጀንሲዎች እና በየመን ለተመድ ልዩ መልእክተኛ ሲሰሩ ነበር።
"ደህንነታቸው ተጠብቆ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በተቻለ ፍጥነት እንዲለቀቁ ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን" ያሉት ዱጃሪክ ተመድ ሰራኞቹን ያሉበትን ሁኔታ ማየት እንደሚፈልግም አክለው ገልጸዋል።
የሀውቲ የደህንነት ታጣቂዎች ባደረጉት ተከታታይ ወረራ ቢያንስ ዘጠኝ የተመድ ስራተኞችን፣ስሶት በአሜሪካ የሚደገፈው የናሽናል ዲሞክራሲ ኢንስቲትዩት (ኤንዲአይ) ሰራተኞችን እና ሶስት የሀገር በቀል የሰብአዊ መብት ድርጅት ሰራተኞችን ማሰራቸውን አለምአቀፍ እውቅና ያለው የየመን መንግስት አስታውቋል።
ዋና ከተማዋን ሰነአን እና አብዛኛውን ሰሜናዊ የየመን ክፍል የተቆጣጠሩት የሀውቲ ደህንነቶች የእነዚህን ሰራተኞች ቤት እና ቢሮ በመበርበር ስልኮቻቸውን እና ኮምፒውተሮቻቸውን ወርሰውባቸዋል።
አለምአቀፍ እውቅና ያለው መንግስት አብዛኛውን ደቡባዊ የየመን ክፍል ይቆጣጠራል።
የሀውቲ ታጣቂዎች በዚህ ጉዳይ መልስ አልሰጡም ተብሏል።
የሀውቲ ታጣቂዎች፣ ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ አጋርነት ለማሳየት በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ ከባለፈው ህዳር ወዲህ ጥቃት እያደረሱ ናቸው። አሜሪካ እና እንግሊዝ ደግሞ ይህን ጥቃት ለማስቆም በማሰብ በሀውቲ ይዞታቸዎች ላይ የአየር ድብደባ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።