የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎች ምን ያህል ዋጋ አላቸው?
በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ እየተሰጡ ያሉ እያንዳንዳቸው የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለመስራት 950 ዶላር ወጪ ተደርጎባቸዋል
በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ሙሉ ለሙሉ ከወርቅ የተሰሩ ሜዳሊያዎችን መስጠት ከቆመ 100 ዓመት አልፎታል
የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎች ምን ያህል ዋጋ አላቸው?
በየ አራት አመቱ አንዴ የሚካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ ሲካሄድ 10ኛ ቀኑን ይዟል።
206 ሀገራት በሚሳተፉበት በዘንድሮው ውድድር ከ10 ሺህ 500 በላይ አትሌቶችም እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡
ሀገራት ከውድድሩ ተሳትፎ የዘለለ ስኬት ማስመዝገብ የሚፈልጉ ሲሆን ዋናው ደግሞ ሜዳሊያዎችን በማንሳት የሀገራቸውን ስም በዓለም አደባባይ ማስተዋወቅ ነው፡፡
ስኬታማ ለሆኑ አትሌቶች ከሚሰጡ ስጦታዎች መካከል ዋነኛው የወርቅ፣ ብር እና ነሀስ ሜዳሊያዎች ናቸው፡፡
ለመሆኑ ስፖርተኞች ብዙ ወጪ አውጥተው፣ ከልምምድ ጀምሮ የሚወጣ ጊዜያቸውን ሰውተው የሚወዳደሩለት እና በመጨረሻም አሸናፊዎች የሚያገኙት ሜዳሊያ ምን ያህል ዋጋ አለው የሚለውን ለብዙዎች ግራ ነው፡፡
በፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ላይ የታዩ ዋና ዋና ስህተቶች ምን ምን ናቸው?
ፎርብስ መጽሄት በኦሎምፒክ ላይ ለአሸናፊዎች የሚሰጡ ሜዳሊያዎች ምንድን ነው ሲል ዝርዝር ዘገባ ሰርቷል፡፡
የኦሎምፒክ ውድድር በየ አራት ዓመቱ አንዴ ሲዘጋጅ ለአሸናፊዎች የሚሰጠው ሜዳሊያ መስሪያ ዋጋ በየዓመቱ እየጨመረ መጥቷል፡፡
በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ አንደኛ ለሚወጡ ስፖርተኞች የሚሰጠው የወርቅ ሜዳሊያን ለመስራት 950 ዶላር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡
529 ግራም የሚመዝነው ይህ የወርቅ ሜዳሊያ 95 በመቶ ህሉ ከብር ማዕድን የተሰራ ሲሆን ስድስት ግራሙ ደግሞ ወርቅ ነው ተብሏል፡፡
በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ የሚሰጠው የወርቅ ሜዳሊያ ሙሉ ለሙሉ ከወርቅ የተሰራ ሜዳሊያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰራው ከ112 ዓመት በፊት በ1912 እንደነበር ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ አንደኛ ለሚወጡ ስፖርተኞች ሙሉ ለሙሉ ከወርቅ የተሰራ ሜዳሊያ ለመስጠት 41 ሺህ 161 ዶላር ወጪ ይጠይቅ ነበር ተብሏል፡፡
486 ዶላር ዋጋ ያለው እና ሁለተኛ ለሚወጡ ስፖርተኞች የሚሰጠው የብር ሜዳሊያ 507 ግራም ካለው የብር ጌጥ ሲሆን 18 ግራም ደግሞ ብረት ነው፡፡
እንዲሁም 13 ዶላር ዋጋ ይፈጃል የተባለው የነሀስ ሜዳሊያ አብዛኛው መጠኑ በመዳብ የተሰራ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ብረት እንደሆነ ተገልጿል፡፡