በስፖርቱ አለም ታዋቂውን የኦሎምፒክ አርማ ያስተዋወቁት ፈረንሳዊው ፒር ደ ኩበርቲን ናቸው
አምስት የተለያየ ቀለማት ያሏቸው ቀለበቶች የተሳሰሩበት የኦሎምፒክ አርማ በአለማቀፍ ደረጃ እውቅናን ካተረፉ የስፖርት መለያዎች ውስጥ አንዱ ነው።
በነጭ መደብ ላይ የሚያርፉት ቀለበቶች በ1912ቱ የስቶኮልም ኦሎምፒክ የተሳተፉ አምስት የአለማችን ክፍሎችን ይወክላሉ።
ጥቁር ቀለም ያለው ቀለበት አፍሪካን፤ ቢጫው እስያን፤ ሰማያዊው አውሮፓን፤ ቀዩ ደግሞ ደቡብና ሰሜን አሜሪካን እንዲወክሉ ተደርጓል።
ዝነኛውን የኦሎምፒክ አርማ ዲዛይን ያስተዋወቁት ፈረንሳዊው የታሪክ ተመራማሪ ፒር ደ ኩበርቲን ናቸው።
የአለማችን ሀገራት ሰንደቅ አላማዎቹ ከአምስቱ የቀለበቶቹ ቀለማትና ነጩን መደብ ቢያንስ አንዱን የሚይዙ መሆናቸውም የኦሎምፒኩ አርማ ከ100 አመታት በላይ ዝነኛና ተወዳጅ ሆኖ እንዲቀጥል እንዳደረገው ይነገራል።