የአለምአቀፉ ፍ/ቤት አቃቤ ህግ በሱዳን ዳርፉር የጦር ወንጀል እየተፈጸመ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናገሩ
ባለፈው ታህሳስ ወር አሜሪካ የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ስትል በይፋ ፈርጃለች
ወንጀሎቹ የተፈጸሙት በዳርፉር ግዛት በኢል ጀኒና ከተማ እና አካባቢ መሆኑን አቃቤ ህጉ 15 አባላት ላሉት የጸጥታው ምክር ቤት አስረድተዋል
የአለምአቀፉ ፍ/ቤት አቃቤ ህግ በሱዳን ዳርፉር የጦር ወንጀል እየተፈጸመ ነው ብል እንደሚያምን ተናገረ።
የአለምአቀፉ ፍ/ቤት አቃቤ ህግ በሱዳን ዳርፉር ግዛት የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የጦር ወንጀል እየፈጸሙ ነው ብሎ ለማመን የሚያስችል መነሻ ምክንያት መኖሩ ለተመድ የጸጥታው ምክርቤት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
በሚያዝያ አጋማሽ 2023 በሱዳን፣ በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ በንጹሃን ግፎች መፈጸማቸው ይነሳል።
የፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ካሪም ካን በዳርፉር ግዛት እየጨመረ በመጣው ጥቃት ላይ ባለፈው ሀምሌ ወር ነበር ምርመራ የከፈቱት።
የፍርድ ቤቱ ማቋቋሚ ስምምነት፣ ፍርድ ቤቱ የዘርማጥፋት ወንጀልን፣ በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀልን፣ ወረራን እና የጦር ወንጀልን የመዳኘት ስልጣን አለው።
ካን በእሻቸው ግኝት እና ግምገማ መሰረት የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በዳፉር ግዛት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
ወንጀሎቹ የተፈጸሙት በዳርፉር ግዛት በኢል ጀኒና ከተማ እና አካባቢ መሆኑን አቃቤ ህጉ 15 አባላት ላሉት የጸጥታው ምክር ቤት አስረድተዋል።
ካን እንደገለጹት "የተጠቀሱት ወንጀሎች መፈጸማቸውን የሚያስረዱ ቁሳቁሶች፣ መረጃዎች እና ማስረጃዎች እየሰበሰብን ነው" ብለዋል።
ባለፈው አመት በኢል ጀኒና በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት ከ10ሺ- 15ሺ የሚሆኑ የማሳሊት ጎሳ አባለት በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና በተባባሪ የአረብ ሚሊሻዎች መገደላቸውን ሮይተርስ ለተመድ ቀርቧል ያለውን ሪፖርት ጠቅሶ በዚህ ወር መጀመሪያ መዘገቡ ይታወሳል።
ባለፈው ታህሳስ ወር አሜሪካ የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ስትል በይፋ ፈርጃለች።
የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ግን ወንጀል አልፈጸምንም ሲሉ አስተባብለዋል።