እስራኤል ከዌስትባንክ ከተማዋ ጀኒን ዛሬ ጦሯን ማስወታት ጀምራለች
የእስራኤል ጦር በዛሬው እለት በጋዛ የሃማስ የጦር መሳሪያ ማምረቻን በጄት መምታቱን ገልጿል።
ጦሩ የሃማስን የምድር ውስጥ መሳሪያ ማምረቻና ማከማቻ ሲመታ የሚያሳይ ምስልንም አውጥቷል።
ለሁለት ቀናት በጀኒን ከተማ “ሽብርተኞችን የማጥፋት ዘመቻ” ማካሄዷን የገለጸችው ቴል አቪቭ፥ ጦሯን ከከተማዋ ማስወጣት መጀምሯን ሬውተርስ ዘግቧል።
ሃማስም ለዚህ ዘመቻ አጻፍውን ለመመለስ ሮኬቶችን ማስወንጨፉና ጉዳት ሳያደርሱ እንዲከሽፉ መደረጋቸውን ነው የእስራኤል ጦር የገለጸው።
እስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢንያሚን ኔታንያሁ ዳግም ወደስልጣን ከተመለሱ ወዲህ በፍልስጤም በሚገኙ ታጣቂ ሃይሎች ላይ የተጠናከረ እርምጃ እየወሰደች ነው።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic