ማሻሻያው ለመንግስት ዳኞችን የመምረጥና የጠቅላይ ፍርድቤት ስልጣንን የመቀነስ ስልጣን ይሰጣል ተብሏል
በእስራኤል የፍትህ ስርአት ማሻሻያው ላይ የአደባባይ ተቃውሞው ቀጥሏል።
ትናንት ምሽትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን በቴልአቪቭ ጎዳናዎች ወጥተው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በመጋቢት ወር ያስተዋወቁት የፍትህ ማሻሻያ ለ26ኛ ሳምንት ነው ተቃውሞ ያስተናገደው።
ማሻሻያው ለመንግስት ዳኞችን የመምረጥና የጠቅላይ ፍርድቤት ስልጣንን የመቀነስ ስልጣን ይሰጣል ተብሏል።
በዚህ ተቃውሞ በበረታበት የፍትህ ማሻሻያ ዙሪያ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር የተደረገው ውይይት ውጤት እንዳልተገኘበት ኔታንያሁ ባለፈው ሳምንት መግለጻቸው ይታወሳል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic