ፍልስጤማውያን ሁለት የእስራኤል ድሮኖችን መጣላቸውን ገልጸዋል
እስራኤል በሰሜናዊ ዌስትባንክ በምትገኘው ጀኒን ከተማ በድሮን ጥቃት ፈጽማለች።
የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በጥቃቱ እስካሁን ስምንት ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን፥ ከ20 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
የእስራኤል ጦር በበኩሉ “ሽብርተኞች የተሰባሰቡበት” ነው ያለውን የጀኒን የስደተኞች ካምፕ ኢላማ አድርጎ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።
ከ6 በላይ ድሮኖች እና ከ1 ሺህ በላይ እግረኛ ወታደሮች ትናንት በጀመሩት የተቀናጀ ዘመቻ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ውድመት ደርሷል።
ፍልስጤማውያን በጀኒን ጥቃት ሲፈጽሙ ከነበሩት ድሮኖች ሁለቱን መተው መጣላቸውን የሚያሳዩ ምስሎች ለቀዋል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic