ኢራቅ በአሜሪካ የሚመራውንተ ተልዕኮ ለመዝጋት እየተዘጋጀሁ ነው አለች
አሜሪካ ሊዚሁ ተልእኮ በሶሪያ 900 እና በኢራቅ ደግሞ 2500 ወታደሮችን አሰማርታለች
በአሜሪካ የሚመራውን ጥምረት ተልዕኮ ለመዝጋት ኮሚቴ ማቋቋሟን የጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሺያ አልሱዳኒ ቢሮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል
ኢራቅ በአሜሪካ የሚመራውን ጥምረት ተልዕኮ ለመዝጋት እየተዘጋጀሁ ነው አለች።
የኢራቅ መንግስት በሀገሪቱ የሚገኘውን በአሜሪካ የሚመራውን ጥምረት ተልዕኮ ለመዝጋት ኮሚቴ ማቋቋሟን የጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሺያ አልሱዳኒ ቢሮ በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የሱዳኒ ቢሮ መግለጫ ያወጣው በአሜሪካ በባግዳድ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት የሚሊሻ መሪ መገደሉን ተከትሎ ነው።
ይህ የአሜሪካ ጥቃት፣ ተልእኮው እንዲዘጋ መንግስትን ሲጠይቅ የነበረውን በኢራን የሚደገፈውን ቡድን አበሳጭቷል።
መግለጫው "መንግስት በኢራቅ ያለውን አለምአቀፍ ጥምረት በዘላቂነት በመዝጋት ጉዳይ የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም ቀን ቆርጧል" ብሏል።
ኮሚቴው ከወታደራዊ ጥምረቱ እና ከመንግስት ባለስልጣናት ተወካዮችን ያካትታል ተብሏል።
ፔንታጎን እንደገለጸው የአሜሪካ ጦር ባለፈው ሀሙስ ጥቃት የፈጸመው በአሜሪካ ፐርሶኔሎች ላይ የደረሰውኝ ጥቃት ለመበቀል ነው።
አሜሪካ ከመሸነፉ በፊት በሶሪያ እና በኢራቅ በመንቀሳቀስ ሰፊ ቦታ መያዝ የቻለውን አይኤስን ለሚዋጉት የሁለቱ ሀገሪት ኃይሎች ለማማከር እና ለመርዳት በሚል ነበር ወታደሮቿን የላከችው።
አሜሪካ ሊዚሁ ተልእኮ በሶሪያ 900 እና በኢራቅ ደግሞ 2500 ወታደሮችን አሰማርታለች።
በኢራን የሚደገፉት በኢራቅ እና በሶሪያ የሚንቀሳቀሱት ታጣቂ ቡድኖች እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ዘመቻ ይቃወማሉ፤ በተወሰነ መልኩ አሜሪካንም ተጠያቂ ያደርጋሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሱዳኒ በኢራን ይደገፋሉ ከሚባሉት ታጣቂ ቡድኖች ውስጥ የተወሰኑትን ይቆጣጠራሉ።
"ጥምረት ያስፈለገበት ሁኔታ አሁን ላይ ባለመኖሩ፣ አለምአቀፍ ጥምረቱ እንዲዘጋ ግልጽ አቋም ይዘናል" ማለታቸውን መግለጫው ጠቅሷል።
አይኤስ በኢራን የ100 ሰው ህይወት ለቀጠፉት የኢራን ሁለት ፍንዳታዎች ኃላፊነት ወስዷል።