ኢራቃዊቷ የቲክቶክ ተጽዕኖ ፈጣሪ ኦም ፋሀድ በጥይት ተገደለች
የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር የግድያውን ሁኔታ ለማጣራት የምርመራ ቡድን ማቋቋሙን ገልጿል
በቲክቶክ በምትለቃቸው ቪዲዮዎች ታዋቂነትን ያተረፈችው ኢራቃዊቷ ኦም ፋሀድ ባግዳድ ውስጥ በጥይት ግድያ ተፈጽሞባታል
በቲክቶክ በምትለቃቸው ቪዲዮዎች ታዋቂነትን ያተረፈችው ኢራቃዊቷ ኦም ፋሀድ ባግዳድ ውስጥ በጥይት ግድያ ተፈጽሞባታል።
በሺዎቹ የሚቆጠሩ የቲክቶክ ተከታዮቿ ኦም ፋሀድ በሚለው ስሟ የሚያውቋት የቲክቶክ ኮከብ በምስራቃዊ ባግዳድ ዛዮና ግዛት በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ደጃፍ በጥይት መገደሏን መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል።
በደህንነት ካሜሪ የተቀረጸው ቪዲዮ ጥቁር የለበሰ እና ሄልሜት(ቆብ) ያጠለቀ አጥቂ ከሞተርሳይክል በመውረዳ ወደ ኦም ፋሀድ ሄዶ ሲተኩስባት ያሳያል።
የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር የግድያውን ሁኔታ ለማጣራት የምርመራ ቡድን ማቋቋሙን ገልጿል።
በትክክለኛ ስሟ ጉፍሳን ሳዋዲ ተብላ የምትጠራው ኦሞ ፋሀድ በፖፕ ሙዚቃ እየደነሰች በምትለቃቸው ቪዲዮዎች ቲክቶክ ላይ ተወዳጅ በመሆን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተከታዮች አፍርታለች።
ፍርድ ቤት ኦም ፋሀድ የለቀቀቻቸው ቪዲዮዎች ጨዋነት የጎደላቸው ስለሆኑ የህዝብን የሞራል እሴት ይሸረሽራሉ በሚል በየካቲት 2023 የስድስት ወር እስር አስተላልፎባት ነበር። ከለቀቀቻቸው ውስጥ አንዳንድ ቪዲዮዎች ከ1ሚሊዮን ጊዜ በላይ የታዩ ይገኙበታል።
በጊዜው ተጨማሪ አምስት 'ኮንቴንት ክሬተርስ' ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት አዘጋጆች እስከ ሁለት አመት በሚደርስ እስራት ተቀጥተዋል።
ይህ የሆነው የኢራቅ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር በኢራቅ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉትን "ሞራልን እና የቤተሰብ ባህልን" እንደ ኦም ፋሀድ በመሳሰሉ ተጽእኖ ፈጣሪዎች በኦንላይን ከሚፖሰቱ "አስቀያሚ እና ክብረነክ" ይዘቶች ለመጠበቅ በ2023 ኮሚቴ ማቋቋሙን ተከትሎ ነው።
ሚኒስቴሩ ኢራቃውያን እንዲህ አይነት ይዘቶች እንዲሰረዙ ሪፖርት የሚያደርጉበትን የኦንላይን ፕላትፎም አዘጋጅቶም ነበር። በጊዜው ባለስልጣናቱ ህዝቡ የኦንላይን ፕላትፎርሙን በበጎ እንደተቀበለው እና በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ሪፓርቶች እንደተመዘገቡ ገልጸዋል።
መንግስት እርምጃ ከወሰደ በኋላ ተወሰኑ የይዘት አዘጋጆች ይቅርታ እንዲጠይቁ እና በኦንላይን የለቀቁትን ይዘት እንዲያጠፉ ተገደውም ነበር።
በመቀመጫውን ጀኔቫ ያደረገው ዩሮ ሜድ ሂማን ራይትስ ሞኒተር ባለፈው አመት ባወጣው ሪፖርት ኦም ፋሀድን በማነሰሳት ለመክሰስ የሚያስችል የህግ መሰረት አለመኖሩን እና የፖሰተቻቸው ይዘቶችም ከመናገር ነጻነት ገደብ ያለፉ አይደሉም ብሎ ነበር።