የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በግድቡ ድርድር ሊያሳድር የሚችለው ተጽዕኖ የለም- የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር
የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ሰኔ ላይ ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ መባሉ የሚታወስ ነው
ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ይቀጥል የሚል ፍላጎት አሁንም በሃገራቸው ዘንድ እንዳለ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በግድቡ የድርድር ሂደት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ቀጥተኛ ተጽዕኖ የለም- የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር
ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው የህግ ማስከበር እርምጃ በግድቡ የድርድር ሂደት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ቀጥተኛ ተጽዕኖ እንደሌለ የሱዳን የመስኖ እና የውሃ ሃብት ሚኒስትር ያሲር አባስ (ፕ/ር) ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ ትናንት በጁባ የሰላም ስምምነት ለተፈራረሙ የሱዳን ተቀናቃኝ የፖለቲካ ኃይሎች የድርድሩን ሂደት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ገለጻውን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው የህግ ማስከበር እርምጃ በድርድሩ ሂደት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እንደማይኖረው አስረግጠዋል፡፡
ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በአዲስ የአካሄድ ዘዴ ይቀጥል የሚል ፍላጎት አሁንም በሃገራቸው ዘንድ እንዳለም አባስ አስረግጠው የተናገሩት፡፡
አባስ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ግድቡን በተመለከተ ከትራምፕ የተለየ የፖሊሲ አተያይ ሊኖራቸው እንደሚችል ስለመናገራቸውም የሃገሪቱ የዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ የግድቡ ሁለት ተርባይኖች በመጪው ወርሃ ሰኔ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምሩ ማስታወቋ የሚታወስ ነው፡፡