የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴሮች “የሱዳን ወገን” የድርድሩ አካሄድ ካልተለወጠ “አልሳተፍም” ማለቱን አስታውቀዋል
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴሮች “የሱዳን ወገን” የድርድሩ አካሄድ ካልተለወጠ “አልሳተፍም” ማለቱን አስታውቀዋል
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይና የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴሮች ባወጡት የጋራ መግለጫ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን ግብጽ በግድቡ ዙሪያ በበይነ መረብ አማካኝነት የሶስትዮች ድርድር ማካሄዳቸውን አስታውቋል፡፡
መግለጫው የሶስትዮች ድርድሩ በደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትርና በአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክርቤት ሊቀመንበር ሰብሳቢነት መካሄዱንና ሱዳን የድርድሩ አካሄዱ ካልተለወጠ አልሳተፍም ማለቷን ጠቅሷል፡፡
እንደመግለጫው ከሆነ ሱዳን አካሄዱ ካልተለወጠ አልሳተፍም ብትልም የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሀገራቱ በ10 ቀናት ውስጥ ለመሪዎች የሚቀርብ ውጤት ላይ እንዲደርሱ አሳስበዋል፡፡
መግለጫው የግድቡን ውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ የተጀመሪውን ድርድር ማስቀጠል አስፋላጊ መሆኑ ላይ ተስማምተዋል፡፡
ድርድሩ በኢትዮጵያ ሰብሳቢነት በቀጣይ ቀናት እንደሚካሄድም መግለጫው ገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን ሲያካሄዱት የነበረውን ድርድር ኢትዮጵያ ባለመስማማቷ ምክንያት ከተቋረጡ በኋላ ሶስቱ ሀገራት በአፍሪካ ህብረት ማእቀፍ እየተደራደሩ ይገኛሉ፡፡
በዋሽንግተኑ ድርድር በታዛቢነት የገባችው አሜሪካ ከታዛቢነት ሚናዋ ወደ አደራዳሪነት፤አደራዳሪነት ወደ ስምምነት ሰነድ አርቃቂነት ከፍ በማለቱ ምክያነት ኢትዮጵያ ድርድሩን ለማቋረጥ መገደዷን በወቅቱ ገልጸ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ባለፈው ክረምት ወቅት 4.9 ሚሊዮን ኪቡክ ሜትር ውሃ ግድቡ መጀመሪያ ምእራፍ እንዲይዝ አድርጋለች፤ በዚህ አመት ክረምትም ሁለተኛው ምእራፍ ሙሌት እንደሚከወን ገልጿለች፡፡
ግብጽና ሱዳን ኢትዮጵያ በራሷ ውሳኔ ግድቡን መሙላት እንደሌለባት ቢገልጹም ኢትዮጵያ ውሃ መሙላቷን ይፋ ማድረጓ ይታወሳል፡፡