ሞስኮ የአጭር ርቀት ሚሳኤል ማስወንጨፊያውን በዩክሬን ጦርነት እየተጠቀመችበት ነው
“ኢስካንደር -ኤም” የተሰኘው የሩሲያ አጭር ርቀት ሚሳኤል ማስወንጨፊያ ማሻሻያ ተደርጎለት በካሊንግራድ ሙከራ አድርጓል።
ተንቀሳቃሹ ሚሳኤል ማስወንጨፊያ እስከ 500 ኪሎሜትር ድረስ ኢላማውን ያወድማል ተብሏል።
ሞስኮ በዩክሬን የጦር መሳሪያ ማከማቻዎችን፣ የኮማንድ ፓስት ወይም ማዘዣ ጣቢያዎችን እንዲሁም የሚሳኤል ማከማቻ ስፍራዎችን በ“ኢስካንደር -ኤም” ስትመታ ቆይታለች።
በአሁኑ ወቅትም የኒዩክሌር አረር ማስወንጨፍ እንዲችል የተደረገ ሲሆን፥ በዩክሬኑ ጦርነት በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውል መዘጋጀቱ ተነግሯል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic