በ12 ሰከንድ ውስጥ 24 ሮኬቶችን የሚተኩሰው የሩሲያው ጦር መሳሪያ
"ሶልንጺፒዩክ" የተሰኘው ይህ ጦር መሳሪያ ለዩክሬን መልሶ ማጥቃት ዋነኛው እንቅፋት ነው ተብሏል
በታንክ ላይ በመግጠም ይተኮሳል የተባለው ይህ የጦር መሳሪያ በአንድ ጊዜ 40 ሺህ ስኩየር ሜትር ቦታ ላይ ያለ ኢላማ የማውደም አቅም አለው
በ12 ሰከንድ ውስጥ 24 ሮኬቶችን የሚተኩሰው የሩሲያው ጦር መሳሪያ....
ከ520 ቀን በላይ ያስቆጠረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት መልኩን በየጊዜው እየቀያየረ ይገኛል።
ሩሲያ አሁን ድረስ 17 በመቶ የዩክሬንን መሬት እንደያዘች ሲሆን ዩክሬን ከምዕራባዊያን ባገኘቻቸው የጦር መሳሪያዎች አዲስ ጥቃት መክፈቷን አስታውቃለች።
ሩሲያ በዩክሬን የተከፈተባትን አዲስ ጥቃት እየመከተች ሲሆን "ሶልንጺፒዩክ" የተሰኘው የጦር መሳሪያ ዋነኛው ጥቃት ማክሸፊያ መሳሪያ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ የጦር መሳሪያ በፈረንጆቹ 2001 ላይ የተሰራ ቢሆንም የሩሲያ ጦር እንደአዲስ በማዘመን ለዩክሬን መልሶ ማጥቃት ማክሸፊያ እያዋለው መሆኑ ተገልጿል።
ይህ የጦር መሳሪያ በአንድ ጊዜ 24 ሮኬቶችን መተኮስ የሚያስችል ሲሆን በ40 ሺህ ስኩየር ቦታ ላይ ያለ ኢላማን ማውደም ይችላል ተብሏል።
እንዲሁም ይህ የጦር መሳሪያ ታንክን ጨምሮ በማንኛውም የጦር መሳሪያ ላይ ተገጥሞ መተኮስ መቻሉ ዩክሬንን እየፈተነ እንደሆነ ተገልጿል።
የሩሲያ መከላከያ እንደገለጸው የዩክሬንን የምድር ላይ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻዎችን እየመከተበት እንደሆነ አስታውቋል።
ሩሲያ በተለይም የዩክሬን የጦር መሳሪያ መጋዝኖችን፣ ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን እና ሌሎች የጠላት መገናኛዎችን እና ይዞታዎች ላይ ቃጠሎ ማድረስ ያስችላልም ተብሏል።