ፖለቲካ
ሩሲያ በዩክሬን የያዝኩት ዓላማ የሚሳካው በወታደራዊ ኃይል ብቻ ነው አለች
ሀገሪቱ ሩሲያኛ ተናጋሪዎችን “ነጻ ለማውጣት” በዩክሬን እየተዋጋሁ ነው ብላለች
ኪየቭ የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬንን ግዛት ለቀው ከወጡ በኋላ ስለ ሰላም ስምምነት አስባለሁ ብላለች
ክሬምሊን እንዳስታወቀው በኪየቭ አቋም መሰረት ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ ያላትን ግብ ማሳካት የሚቻለው በወታደራዊ ኃይል ብቻ ነው።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ "ግባችንን ማሳካት አለብን፤ የኪየቭ አገዛዝ አሁን ባለው አቋም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ይህ የሚቻለው በወታደራዊ መንገድ ብቻ ነው" ብለዋል።
ሩሲያ ኒዮ-ናዚ ብላ ከጠራችው የኪየቭ አገዛዝ በምስራቃዊ ዶንባስ የሚገኙ ሩሲያኛ ተናጋሪዎችን “ነጻ ለማውጣት” በዩክሬን እየተዋጋሁ ነው ማለቷን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዩክሬን እና ምዕራባውያን ይህ የጥቃት ጦርነት ምክንያት የለሽ ሰበብ ነው፤ ሞስኮ የዩክሬንን መሬት ለመቀማት የምታደርገው ሙከራ ነው ይላሉ።
ሞስኮ የተኩስ አቁም ስምምነት ፍሬ አለመፍራት ኪየቭን ተጠያቂ አድርጋለች።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬንን ግዛት ለቀው ከወጡ በኋላ ስለ ሰላም ንግግሮች እንደሚያስቡ ተናግረዋል።