እስራኤል በየመን ላይ ጥቃት የከፈተችው ሃውቲ የእስራኤል ኤርፖርት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ነው
የእስራኤል ጦር በምእራባዊ የመን በሚገኙት ራስ ኢሳ እና ሆዴዲያህ አካባቢዎች ላይ የአየር ድብደባ መክፈቱ ተገለጸ።
እስራኤል በምእራብ የመን ላይ ጥቃት የከፈተው የየመኑ ሃውቲ በቴል አቪቭ ቤን ጉሪዮን ኤርፖርት ላይ ሚሳዔል ከተኮሰ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
የእስራኤል ጦር ባወጣው መግለጫ ተዋጊ ጄቶቹ በየመን በሚገኙ የሃውቲ ኢላማዎች ላይ የአየር ድብደባ እያደረጉ መሆኑን አስታውቋል።
ጦሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የእስራኤል የአየር ድብደባ ራስ ኢሳ እና ሆዴዲያህ የሚገኙ የሃውቲ ታጣቂዎች ይዞታን ኢላማ አድርጎ እንደሚፈጸም ገልጿል።
በየመኑ ሃውቲ የሚመራው ማሲራህ ጣቢያም የእስራኤል ጦር ጄቶች ራስ ኢሳ እና ሆዴዲያህ ወደቦች እንዲሁም በተወሰኑ የኤሌክትሪክ ኃይል ጣቢያዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራውን አስታውቋል።
የየመኑ ታጣቂ ቡድን ሃውቲ አብዛኛውን ሰሜናዊ የሀገሪቱን ክፍል ተቆጣጥሮ የሚገኝ ሲሆን፤ በእስራል ላይ የረጅም ርቀት ሚሳዔሎችን ተጠቅሞ በተለያዩ ጊዜያት ጥቃቶችን ሰንዝሯል።
ሃውቱ የእስራኤል ጋራ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ደግሞ በቀይ ባህር ላይ በሚጓዙ እና ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ባላቸው መርከቦች ላይ ጥቃቶችን ሲሰነዝር ቆይቷል።
አሜሪካ እና እንግሊዝን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራትም ከመርከቦች ጥቃት ጋር በተያያዘ በተለያዩ ጊዜያት በሀውቲ ይዞታዎች ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል።