አሜሪካ፣ጃፓን እና አውስትራሊያ በሩሲያ ላይ ማእቀብ ሲጥሉ ህንድ ትልቅ የጦር መሳሪያ አቅራቢዋ በሆነቸው ሩሲያ ላይ ማእቀብ አልጣለችም
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከካድሪላቶራል ሴኩሪቲ ዲያሎግ(ቁአድ) ቡድን ሀገራት መካከል ህንድ፣ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ጦርነት ለመቃወም በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም ድፍረት ማጣቷን ተናግረዋል፡፡ ህንድ በምእራባውያንና በሩሲያ መካከል ሚዛናዊ የሆነ ግንኙነቷን ለማስቀጠል እየሞከረች መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሌሎች የቁአድ ሀገራት ማለትም አሜሪካ፣ጃፓን እና አውስትራሊያ በሩሲያ ላይ ማእቀብ ሲጥሉ ህንድ ትልቅ የጦር መሳሪያ አቅራቢዋ በሆነቸው ሩሲያ ላይ ማእቀብ አልጣለችም፡፡
ህንድ በዩክሬን ያለው ጦርነት እንዲያበቃ ብትጠቅይም፤የቀዝቃዛው ጦርነት አጋሯ በዩክሬን ያደረገችውን ወረራ አወገዘችም፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት እና በፓስፊክ በኩል ለወረራው አጸፋ የሚሆን ግንባር መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡
ከቁአድ ቡድን ሀገራት መካከል ጃፓን እና አውስትራሊያ ጠንካራ አቋም ሲያራምዱ፣ ህንድ ግን ሩሲያ እስካሁን ሩሲያን በግልጽ አላወገዘችም፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን “ልዩ ወታደራ ዘመቻ” ለማካሄድ የተገደደችው፤ የዩክሬን መንግስት በዶንባስ ግዛት በሚገኙ የሩሲያኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ላይ “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እየፈጸመ ነው በሚል ነበር፡፡ ምእራባናውን የሩሲያ ክስ አይቀበሉም፡፡
ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ “በዩክሬን የተጀመረው ወታደራዊ ተልዕኮ” ሀገራቸው ባቀደችው መልኩ እየተካሄደ መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
የሩሲያ ጦር እስካሁን ባካሄደው “ዘመቻ” በደቡብ ዩክሬን የምትገኝው ኬርሶን ከተማ ጨምሮ ሌሎች ቦታዎችንና ከተሞችን መቆጣጠር ችሏል፡፡ የሩሲያ ወታራዊ ዘመቻ በምዕራባውያን ዘንድ ያልተወደደ በመሆኑ በርካታ የኢኮኖሚ ማዕቀቦች ጎርፍ እየወረደባት ነው፡፡ ምዕራባውያን የኢኮኖሚ ማእቀብ ከመጣል በተጨማሪ የአየር ክልላቸውን ለሩሲያ ዝግ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት የከፈተችው፣የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ የሶቬት ህብረት ሀገራት እተሰፋፋ ነው፤ይህም ለደህንነቷ አስጊ እንደሚሆን በመግለጽ ነበር።የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እደቀጠለ ቢሆንም ሀገራቱ ችግሩን ለመፍታት ሁለተኛ ውይይታቸውን ጀምረዋል።