ለ7 ቀናት ባልታወቀ ቦታ ታስሮ የነበረው ጋዜጠኛ ጎበዜ በትናንትናው እለት ተፈትቷል
ባልታወቀ ቦታ ለ7 ቀናት ከታሰረ በኋላ በትናንትናው እለት የተለቀቀው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በደረሰበት የእስር ተግባር ምክንያት የጋዜጠኝነት ሙያውን እንደማያቆም ተናግሯል፡፡
ጋዜጠኛ ጎበዜ የታሰረበት አድራሻ መጥፋት በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪ ሆኖ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ጎበዜ የደረሰበትን ህገ-ወጥ ተግባር ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አቤት ማለቱን፤ ጉዳዩን ኮሚሽኑ መያዙን ለአል ዐይን አማርኛ ተናግሯል፡፡
ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በህገወጥ መንገድ መያዙን የገለጸው ጋዜጠኛ ጎበዜ የ”ፋኖ”ን እንቅስቃሴ ይደግፋል የሚል እና ሌሎች ብዙ ክሶች ቀርበውበት እንደነበር ገልጿል፡፡ ከደረሰበት እስር በኋላ በስራ መቀጠል ከባድ ቢሆንም የጋዜጠኝነት ስራውን ከመቀጠል ወደኋላ እንደማይል ተናግሯል፡፡
ለመመከር ዝግጅ መሆኑን የገለጸው ጎበዜ ህገወጥ ተግባር ግን መቆም አለበት ብሏል፡፡
ጋዜጠኛው የታሰርኩት በመንግስት አካላት ነው ብሏል፡፡ ነገርግን መንግስት በዚህ ገዳይ እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንም የጋዜጠና ጎበዜ ሲሳይ መታሰር እና ያለበት አለመታወቅ እንሚያሳስበው መግለጹ ይታወሳል፡፡ ኢሰመኮ በቅርቡ የዓለም የፕሬስ ቀንን ምክያት በማድረግ በሰጠው መግለጫ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ አካላት ያለ ፍትህ ሂደት መታሰራቸው እንደሚያሳስበውም ገልጾ ነበር፡፡