ኢሰመኮ የደረሰውን ሰብአዊ ቀውስ የሚመመረምር ገለልተኛ እና ግልጽ አሰራር እንዲተገበር ጠየቀ
ኮሚሽኑ ከትግራይ ተወላጆች የሚቀርቡልኝ ቅሬታዎች በከፍተኛ ደረጃ እያሳሰቡኝ ይገኛሉም ብሏል
በመልሶ ማቋቋም ተግባራት ለሰብዓዊ መብቶች ቅድሚያ እንዲሰጥም ጠይቋል
ኢሰመኮ የደረሰውን ሰብአዊ ቀውስ የሚመመረምር ገለልተኛ እና ግልጽ አሰራር እንዲተገበር ጠየቀ
በመልሶ ማቋቋም ተግባራት ለሰብዓዊ መብቶች ቅድሚያ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ፡፡
ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የሚደረገው ዘመቻ ተጠናቋል መባሉን ተከትሎ በቀጣይ የሚደረጉ የመልሶ ማቋቋምና መልሶ ግንባታ ተግባራትን የተመለከተ ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫው ተግባራቱ ሰብአዊ መብቶችን በማክበር እና በመጠበቅ ግዴታሊመሩ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙና ተገቢው ሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን ያለም ሲሆን የተቋረጡ የውሃ እና መብራትን መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ አካላት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ጠይቋል፡፡
የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና ያስከተለውን ሰብአዊ ቀውስ የሚመመረምር ገለልተኛና ግልጽ የሆነ አሰራር ከወዲሁ ይተግበርም ነው ኮሚሽኑ ያለው፡፡ ተዓማኒና አካታች የሆኑ የእርቅና የፍትሕ ሂደቶች በጊዜ እንዲደራጁም ጠይቋል።
ኮሚሽኑ በትግራይ ተወላጆች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረገ መገለል እና መድሎዎ መድረሱን በተመለከተ የሚቀርቡልኝ ቅሬታዎች በከፍተኛ ደረጃ እያሳሰቡኝ ይገኛሉም ብሏል፡፡
ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሚገኝ የገለጸም ሲሆን ችግሩ በአፋጣኝ እንደሚቀረፍ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች በጎ ምላሾች መሰጠታቸውንና ምላሾቹን መቀበሉን አስታውቋል።
ካለበቂ ሕጋዊ ምክንያት ማናቸውም ተጓዦች ከጉዞ እንዳይከለከሉም ነው ኮሚሽኑ በጥብቅ ያሰሳሰበው፡፡