አዲሱ ተሽከርካሪ በአሜሪካዊው ቢሊየነር ኢለን መስክ ቴስላ ኩባንያ የተሰራ ነው
ስናይፐር ታጣቂው የቺቺኒያው መሪ አዲስ ተሽከርካሪ
እስማኤል ከዲሮቭ የሩሲያዋ ቺቺንያ ክልል አስተዳዳሪ ናቸው፡፡ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደጋፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ከዲሮቭ የዩክሬን ጦርነትን እየደገፉ ካሉ የክልል መሪዎች መካከል ዋነኛው ሰው ናቸው፡፡
በዛሬው ዕለት የዓለማችን ቀዳሚ ባለጸጋ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው አሜሪካዊው ኢለን መስክ ኩባንያ የሆነው ቴስላ ስሪት አዲ ተሽከርካሪ ጋር ታይተዋል፡፡
ከዲሮቭ ሲያሽከረክሩት የታየው ይህ ተሽከርካሪ ላይ ስናይፐር መሳሪያ የተገጠመለት ሲሆን ክስተቱን የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ብዙ ተመልካች አግኝቷል፡፡
ቺቺኒያ ፈጣን ስልተ ምት ያላቸውን መዚቃዎች አገደች
የቺቺንያ መሪው ከዲሮቭ በዚህ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ስናይፐር የተገጠመለትን አዲስ ቴስላ ተሽከርካሪ ወደ ጦር ግንባር ሊልኩት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ከዲሮቭ አክለውም የቴስላ ኩባንያ መስራቹን ኢለን መስክን እና ኩባንያቸውን ያደነቁ ሲሆን ወደ ቺቺኒያ እንዲመጣ እና እንዲጎበኛቸው እንደሚፈልጉ በቴሌግራም ገጻቸው ላይ ጽፈዋል፡፡
እንዲሁም ቴስላ ኩባንያ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ያለውን ልዩ ዘመቻ በድል ማጠናቀቅ የሚያስችላትን ዘመናዊ ጦር መሳሪያዎች እንዲያመርትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ይሁንና ቴስላ ኩባንያ እስካሁን በቺቺኒያው መሪ እስማኤል ካዲሮቭ ግብዣ እና ንግግር ዙሪያ ምላሽ አልሰጠም፡፡