ሩሲያ ምዕራባውያን ለዩክሬን የሰጧቸው መሳርያዎች መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም እየዋሉ ነው አለች
አሜሪካ ሰራሹ ሂማርስ የተሰኘው ሮኬት መኖርያ ቤቶችን ጨምሮ በመሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም መዋሉ ተሰምቷል
በዛሬው እለት ከዩክሬን ድንበር 10 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ከተማ የዩክሬን ጦር መቆጣጠሩን አስታውቋል
ሩሲያ የምዕራባውያን የጦር መሳርያዎች የሲቪል መሰረተ ልማቶችን ለማጥቃት ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሚገኙ ገለጸች።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ለሰብአዊ መብት መከበር እንቆረቆራለን የሚሉ ምእራባውያን በሩሲያ ላይ ዝምታቸውን መርጠዋል ብለዋል፡፡
ከሳለፍነው ማክሰኞ ጀምሮ ዩክሬን በምእራባዊ ዩክሬን ግዛት ኩርሰክ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ሞስኮ ስለጥቃቱ የምእራባውን እጅ እንዳለበት መናገሯ ይታወሳል፡፡
የአሜሪካ እና ምእራባውያን ለዩክሬን የሚሰጧቸው ጦር መሳርያዎች ጥቅም ላይ ውለውበታል ከተባለው ስፍራ መካከል ኩርስክ ግዛት ሴይም በተባለው ወንዝ ላይ በነበረውን ድልድይ ላይ የተፈጸመው ጥቃት አንዱ ነው ተብሏል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በመግለጫው በጥቃቱ በአካባቢው የሚገኙ ዜጎችን ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ንጹሀን መገደላቸውን ነው ያስታወቀው፡፡
ይህ ድልድድይ በኩርሰክ ግዛት እየተዋጉ ለሚገኙ የሩሲያ ወታደሮች የሎጅስቲክ አቅርቦት የሚተላለፍበት መሆኑ ታውቋል፡፡
ዩክሬን በንጹሀን ላይ ለፈጸመችው ጥቃት በዩክሬን ዛካሮቫ ግዛት ተመጣጣኝ እርምጃ ሞስኮ እንደምትወስድ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ ይፋ አድርጓል፡፡
ዩክሬን ወደ ሩሲያ ዘልቃ መግባቷን ስትቀጥል የሩስያ ቤልጎርድ ግዛት አመራሮች አምስት መንደሮች ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች እንዲወጡ አሳስበዋል።
በዛሬው እለትም ወደ ፊት እየገሰገሰ የሚገኝው የኬቭ ጦር ሱድዛ የተባለች ከተማ መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡
እስከ አምስት ሺ ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ ከዩክሬን ድንበር 10 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ መሆኗም ተሰምቷል፡፡