አፈጉባኤዋ የታሪካዊና ፖለቲካዊ ስህትት አካል ላለመሆን ሲሉ ስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ
ወ/ሮ ኬሪያ የህገ-መንግስት ትርጉም ይሠጥ የሚለው ”ትልቅና ታሪካዊ ስህተት” ነው ብለዋል
የህገ-መንግስት ትርጉም ይሰጥ የሚለውን አማራጭ በመቃወም የፌደሬሽን ምክርቤት አፈ-ጉባኤ ኬሪያ ስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ
የህገ-መንግስት ትርጉም ይሰጥ የሚለውን አማራጭ በመቃወም የፌደሬሽን ምክርቤት አፈ-ጉባኤ ኬሪያ ስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ
የፌደሬሽን ምክርቤት አፈ-ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም በዛሬ እለት በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ይፋ የሚያደርግ በትግራይ ቴሌቪዥን በኩል መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
አፈጉባኤዋ ለዚህ ወሳኔያቸው እንደምክንያት ያቀረቡት መንግስት ስልጣን ለማራዘም የሚያስችል የህገመንግስት አንቀጽ በሌለበት ሁኔታ፤ ስልጣኑንን ለማራዘም ህገ-መንግስት ትርጉም ይሠጥ የሚለው ቀድሞ የተወሰነ፣”ትልቅና ታሪካዊ ስህተት” በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ኬሪያ የታሪካዊና ፖለቲካዊ ስህትት አካል መሆን ስለማይፈልጉ ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውን ገልጸዋል፡፡
“በህገ-መንግስት ትርጉም ሽፋን ፌደራላዊ ስርአት አደጋ ላይ ለሚጥልና ወደ አምባገነናዊ ስርአት ለሚያመራ መንግስት በህገመንግስት ትርጉም ስም የፌደሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ ሆኜ ለማስፈጸም አልፈልግም፤አልተባበርም”ብለዋል፡፡
ህገመንግስት መተርጎም ዋናው አላማ የህገመንግስት ትርጉምን አንደምክንያት ተጠቅሞ አዲስ ህግ ለማውጣት አለመሆኑን ወ/ሮ ኬሪያ ገልጸዋል፡፡
የህገመንግስት ትርጉም አማራጭ”ከወትሮው በተለየ አካሄድ ስልጣን ለማራዘም አማራጭ እየተደረገ” መሆኑንም ወ/ሮ ኬሪያ አስታውቀዋል፡፡
“በራሴ መብት ተጠቅሜ መንግስት በምርጫ እወስናለሁ በሚል ህዝብ[የትግራይ ህዝብ] ላይ የጦርነት ዛቻ“ እየደረሰበት ነው ያሉት ወ/ሮ ኬሪያ “የብሄረሰቦችንና ህዝቦች ቃል ሆነው ህገመንግስት የማስከበር አደራ” ስላለብኝ ህገመንግስቱ ሲጣስ ተባባሪ መሆን እንደሌለባቸው ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ኬሪያ በዘንድሮው አመት ምርጫ አካሂዳለሁ የሚለው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ(ህወሓት) ስራ አስፋፃሚ ኮሜቴ አባል ናቸው፡፡
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት “ምርጫ 2012” በተያዘለት ጊዜ ማካሄድ አልችልም ማለቱን ተከትሎ መንግስትን የሚመራው ብልጽግና ፓርቲ በመራዘሙ ተስማምቶ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የህመንግስትን ትርጉም አንደአማራጭ አቅርቧል፡፡
ይህ አማራጭ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት መጽደቁ የሚታወስ ነው፡፡
ነገርግን ህወሓት በዚህ አይስማማም፤ ብልጽግና ፓርቲ ቀድሞውንም ቢሆን ምርጫውን ለማካሄድ ቁርጠኛ አለመሆኑን ይገልጻል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ህወሓት በትግራይ በሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ላይ ጫና እየፈጠረ ነው የሚል ክስ ያቀርባል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት በፓርላማ ቀርበው መንግስት ለትግራይ ህዝብ ከፍተኛ አክብሮት እንዳለውና ከህወሓት ወይንም ከሌላ ፓርቲ ጋር ሲጋጭ ከትግራይ ህዝብ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል፡፡