10ኛ ቀኑን በያዘው የሱዳኑ ጦርነት ካርቱም በምን ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች?
ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጦሩን በብዛት ወደ ካርቱም እያስገባ ሲሆን፤ የሱዳን ጦር የአየር ድብደባውን ቀጥሎበታል
በርካታ ሱዳናውያን ከሰማይና ከምርድ በሚዘንብ ጥይት ውስጥ ዳቦ ፍለጋና ለሽሽት ሲሯሯጡ ይታያል
በሱዳን ጦር እና ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል እየተከሄደ ያለው ጦርነት 10ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
የጥይት ናዳ በሚዘንብባት ካርቱም ውስጥ የተቃጠሉ የጦር ተሸከርካሪዎች፣ ዳቦ ፍለጋ የሚሯሯጡ ሰዎችን እንዲሁም ጦርነቱን ሽሽትወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚሰደዱ ሰዎችን ማየት የተለመደ ሆኗል።
ጦርነቱ ከዋና ከተማዋ ካርቱም በተጨመሪ የካርቱም ጎረቤት የሆኑትን ባህሪ እና ኦምዱርማን ከተሞች ላይም ተጽእኖ ያሳደረ ሲሆን፤ እነዚህ ሶስት ከተሞች በአጠቃላይ 10 ሚሊየን ገደማ ነዋሪዎን በውስጣቸው የያዙ ናቸው።
የአየር ድብደባ በካርቱም
የአየር ድብደባዎች፣ የከባድ መሳሪያዎች ድብደባ እንዲሁም በክለሽ የሚደረጉ ጦርነቶች ከተማዋን ከጠዋት እስከ ማታ እረፍት ነስተዋታል።
ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጦሩን በብዛት በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ካርቱም እያስገባ በርካታ ህንጻችንም እየተቆጣጠረ መሆኑን የአይን እማኞች ይናገራሉ።
የሱዳን ጦር በበኩሉ ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ኃሎችን ለማስቆም እና ወደኋላ ለመመለስ የአየር ድብደባ እንዲሁም መድፎችን በከተማዋ ውስጥ እየተኮሰ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በጦርነቱ የኤሌክትሪክ እና የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተቋረጠ ሲሆን፤ ሆስፒታሎች ወድመዋል፤ በርካታ ንጹሃን ዜጎችም ከጦርነቱ መሃ መውጫ አጥተው እንደተቸገሩም ነው የተነገረው።
ዳቦ ፍለጋ እና የጦርነት ሽሽት
በዋና ከተማዋ ለ10ኛ ቀን የቀጠለው የአየር ድበደባን ተከትሎ የዳቦ መጋገሪያዎች ስራ ያቆሙ ሲሆን፤ ለዚህም ዋነኛ ምክንያታቸው የዱቄት አቅርቦት እጥረት ነው ተብሏል።
አሁን ባለው ሁኔታ አንድ ፍሬ ዳቦ ማግኘት የህልም እንጀራ እንደሆነባቸውም ነው የካርቱም ነዋሪዎች የሚናገሩት።
በሱዳን ካርቱም የዱቄት እና ሌሎችም መሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆ የመጣ ሲሆን፤ የአትክልት እጥረት እንዳጋጠመ እና ያለውም ዋጋው እጅግ እየተወደደ እንደሆነም ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ባህሪ የተባለው የካርቱ ትልቁ ገበያም በአየር ድበደባው እና በጦርቱ በርካታ ሱቆች መውደማቸው እና በእሳት መቃጠላቸውን ነዋሪዎቸ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሚበላ ያጡና ጦርነት ያሰጋቸው በርካታ ሱዳናውያን ሽሽትን እንደ ዋነኛ አማራጭ የወሰዱት ሲሆን፤ አነስተኛ ሻንጣ ይዘው መንገድ ላይ የሚሄዱ ሰዎችን ማየትም የተለመደ ሆኗል።
ከካርቱም ማእከላዊ አካባቢ ራቅ ያሉ ስፍራዎች ላይ በርካታ ባሶች ጦርነት የሸሹ ሱዳናዎያንን በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በመኩል ወደ ግብጽ እና ወደ ሌሎችም አካባቢዎች ለማጓጓ በዝግጅት ላይ ይገኛሉም ተብሏል።
በተጨማሪም ከካርቱም ከተማ በርካቶች ሻንጣ ይዘው በመንገድ ላይ የሚጓዙ መኪናዎችን እየለመኑ እንዲሁም በሚኒባሶች እየተሳፈሩ እየሸሹ ነውም ተብሏል።