የሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን እንደሚባለው ሱዳን ውስጥ አለ? ምንስ እያደረገ ነው?
የሱዳን ጦር “የሩሲያው ዋግነር ቡድን ለጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ ከለላ እየሰጡ ነው” ሲል ይከሳል
ዋግነር ቡድን “አንድም ተዋጊዬ በአሁኑ ወቅት ሱዳን ውስጥ የለም” ሲል የሚቀርብበትን ክስ ውድቅ አድርጓል
ከተጀመረ ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘው የሱዳን ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን፤ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ኃይሎች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ስማቸው ይነሳል።
በሱዳን ጦር እና ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል እየተከሄደ ባለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ስማቸው ከሚነሳው የውጭ ኃይሎች መካከል የሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን አንዱ ነው።
የሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን እንደሚባለው ሱዳን ውስጥ አለ?
የሱዳን ጦር እንዲሁም አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን በሱዳን ውስጥ ተለያዩ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገነው በሚል ክስ ይቀርብበታል።
የሱዳን ጦር ጦርነቱ መቀስቀሱን ተከትሎ ጦርነቱ በተጀመረ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ “የሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዋና አዛዥ ጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ (ሀሜቲ) ከለላ እየሰጠ ነው” ማለቱ ይታወሳል።
ሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን በበኩሉ በአሁን በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ የለኝም ሲል የሚቀርብበትን ክስ ውድቅ አድርጓል።
ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ቅርበት እንዳላቸው የሚነገርላቸው የዋግነር ቡድን መስራች የቭጌኒ ፕሪገዞሂን፤ “በአሁኑ ሰዓት አንድም የዋግነር ቡድን ተዋጊ በሱዳን ውስጥ የለም” ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የቭጌኒ አክለውም የቡድናቸው ተዋጊዎች በሱዳን ውስጥ ከሁለት ዓመታት ወዲህ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አድርገው እንደማያውቁ አስታውቀዋል።
ዋግነር ቡድን በሱዳን ምን ያደርጋል?
ሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን በፈረንጆቹ ከ2017 ጀምሮ በሱዳን ውስጥ መታየት እንደጀመረ ከስፍራው የተገኘው መረጃዎች እና ምስሎቸ ይጠቁማሉ።
ቡድኑ የሱዳን ጦርንተ ማሰልጠን እና በሱዳን የተከከሰቱ አመጾችን ማስቆምን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።
በፈረንጆቹ 2021 ላይ ከዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው ቴሌግራም በለቀቀው ምስል የቡድኑ አሰልጣኖች ለሱዳን ኃይሎች ስልጠና እና የመስክር ወረቀት ሲሰጡ ያመላክታል።
ሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን በሱዳን ውስጥ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን ባይክድም፤ በአሁኑ ጦርነት ውስጥ ግን ምንመ አይነት ተሳትፎ የለኝም በሚል የሚቀርብበትን ክስ ውድቅ አድርጓል።