ኪም “በግርማዊነትዎ የልደት ቀን በዓል ለሚከበረው ብሔራዊ በዓል እንኳን አደረሰዎ“ ብለዋል በመልዕክታቸው
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን 70ኛ የንግስና ዘመናቸውን በማክበር ላይ ላሉት ለብሪታኒያዋ ንግስት ኤል ሳቤጥ የእንኳን አደረሳችሁ የደስታ መግለጫ መልእክት ላኩ።
የንግስት አልሳቤጥ የንግስና ዘመን መከበር ከጀመረ ትናንት አርብ ሁለተኛ ቀኑን አስቆጥሯል፡፡ በጥቅሉ ለአራት ቀናትም ይከበራል፡፡
ክብረ በዓሉን በማስመልከትም ነው ኪም የእንኳን አደረሰዎ የደስታ መግለጫ መልዕክትን ለንግስቷ እና ለብሪታኒያውያን የላኩት፡፡
ኪም በመልዕክታቸው “በግርማዊነትዎ የልደት ቀን በዓል ለሚከበረው ብሔራዊ በዓል እንኳን አደረሰዎ“ ብለዋል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ብሔራዊ ቀኗን የምታከብረው በመስራቿ በኪም ጆንግ ኢል የልደት በዓል ቀን ነው፡፡
መልዕክቱ ከ2 ቀናት በፊት ነው ወደ ንግስቲቱ የተላከው፡፡
ብሪታኒያ እና ሰሜን ኮሪያ ከ22 ዓመታት በፊት ጀምሮ ነው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ማድረግ የጀመሩት፡፡
ሆኖም አውስትራሊያ፣ ካናዳ እና ኒውዚላንድን ጨምሮ 14 ሃገራትን በበላይ ጠባቂነት የሚያስተዳድሩትና ጎረቤቷን ደቡብ ኮሪያን የጎበኙት ንግስት ኤልሳቤጥ ሰሜን ኮሪያን አንድም ቀን ጎብኝተው አያውቁም፡፡