ኢራን ለሩሲያ ሚሳይል እያስታጠቀች ነው ለሚለው ሪፖርት ክሬሚሊን ምን ምላሽ ሰጠ?
ዎልስትሪት ጆርናል በስም ያልጠቀሳቸውን የአሜሪካ እና የአውሮፓ ባለስልጣናት ኢራን ለሩሲያ የአጭር ርቀት ሚሳይል ሰጥታለች ሲል ዘግቦ ነበር
"የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ፔስኮቭ "ከኢራን ጋር ቀልፍ በሆኑ ጉዳዮች ጨምሮ በሁሉም ዘርፎች ትብብራችን እና ንግግራችን እናሳድጋለን" ብለዋል
ኢራን ለሩሲያ የአጭር ርቀት ሚሳይል እያስታጠቀች ነው ለሚለው የዋልስትሪት ዘገባ የተጠየቀው ክሬሚሊን ሩሲያ እና አጋሯ ኢራን ብዙ ጉዳዮች እየተማከሩ ነው ብሏል።
ጆርናሉ በስም ያልጠቀሳቸውን የአሜሪካ እና የአውሮፓ ባለስልጣናት ኢራን ለሩሲያ የአጭር ርቀት ሚሳይል ሰጥታለች ሲል ዘግቦ ነበር።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ሪፖርቱን ማየታቸውን እና ሁሉም እንዲህ አይነት ሪፖርቶች ትክክል አይደሉም የሚል መልስ ሰጥተዋል።
"ኢራን ወሳኝ አጋራችን ነች። ስለዚህ ከኢራን ጋር ቀልፍ በሆኑ ጉዳዮች ጨምሮ በሁሉም ዘርፎች ትብብራችን እና ንግግራችን እናሳድጋለን" ብለዋል ፔስኮብ።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረችበት ከፈረንጆቹ የካቲት 2022 ወዲህ ቴህራን አመት እና ሞስኮ ግንኙነታቸውን አጠናክረዋል። የኢራን ሪቮሉሽናሪ ጋርድ ከፍተኛ አዛዥ የሆኑት ፋዝሎላህ ናዛሪ በዛሬው እለት እንደተናገሩት ኢራን ለሩሲያ ሚሳይል አስተላልፋ ሰጥታለች የሚለው ሪፖርት "የስነልቦና ጦርነት" ነው ማለታቸውን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢራን የባለስቲክ ሚሳይሎችን ለሩሲያ ልታስታጥቅ ነው የሚለው ሪፖርት እንዳሳሰበው ከትናንት በስትያ አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በቴህራን እና በምስኮ መካከል ያለው ጥልቅ ግንኙነት ለዩክሬን፣ የአውሮፓ እና ለመካከለኛው ምስራቅ ስጋት መሆኑን ገልጾ፣ አለምአቀፉ ማህበረሰብ በኢራን እና በሞስኮ ላይ ጫና እንዲያሳድር ጥሪ አቅርቧል።
ባለፈው አርብ የዩክሬን ዋነኛ አጋር የሆነችው አሜሪካም ኢራን ሚሳይል ለሩሲያ አሳልፋ ልትሰጥ ትችላለች የሚል ስጋቷን ገልጻለች።
የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ሲአን ሴቭዋት እንደተናገሩት ማንኛውንም የኢራንን ሚሳይል ለሩሲያ አስተላልፎ የመስጠት ሂደት ኢራን በዩክሬን ላይ ወረራ እያካሄደች ላለችው ሩሲያ የምትሰጠውን ድጋፍ ከፍ የሚያደግ ተግባር ነው።
በተመድ የኢራን ልኡክ በዩክሬን ጉዳይ የኢራን አቋም አልተቀረም ብሏል።
"ኢራን ለጦርነቱ ተሳታፊዎች የጦር መሳሪያ ማቅረብ የሰዎችን ሞት እና የመሰረተልማቶችን ወድመት እንዲጨምር እና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዳይደረስ ያደርጋል ብላ ታስባለች " ብሏል ልኡኩ።
ምዕራባውያን ሀገራት ኢራን እና ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ በድብቅ የጦር መሳሪያ እያቀረቡ ነው የሚል ክስ ያቀርባሉ።ሰሜን ኮሪያ እና ኢራን ይህን ክስ አይቀበሉትም።