ሩሲያ የፕሬዝደንት ፑቲንና ትራምፕ ግንኙነት ሚስጥራዊ እንዲሆን መምረጧ ተገለጸ
ክሬሚሊን የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንና የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ በስልክ ማውራታቸውን ማረጋገጥም ሆነ ማስተባበል እንደማይፈልግ በዛሬው እለት አስታውቋል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/10/243-195753-img-20250210-185720-600_700x400.jpg)
ሩሲያ በየካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ልዩ ያላችውን ዘመቻ ከከፈተች በኋላ የሁለቱ ኑክሌያር የታጠቁ ኃያላን መሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉት ግንኘነት ሚስጥራዊ ሆኗል
ሩሲያ የፕሬዝደንት ፑቲንና ትራምፕ ግንኙነት ሚስጥራዊ እንዲሆን መምረጧ ተገለጸ።
የሩሲያ ቤተመንግስት ክሬሚሊን የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንና የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርነት በማስቅም ጉዳይ በስልክ ማውራታቸውን ማረጋገጥም ሆነ ማስተባበል እንደማይፈልግ በዛሬው እለት አስታውቋል።
ሩሲያ በየካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ልዩ ያላችውን ዘመቻ ከከፈተች በኋላ የሁለቱ ኑክሌያር የታጠቁ ኃያላን መሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉት ግንኘነት ሚስጥራዊ ሆኗል። ዋሽንግተንም ሆነች ሞስኮ በመሪዎቹ ግንኙነት ጉዳይ ግማሽ ወይም ፍንጭ ከመስጠት በስተቀር በዝርዝር ይፋ አላደረጉም።
ትራምፕ በኤየርፎርስ ዋን ላይ ሆነው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከፑቲን ጋር ስላደረገለት ንግግር ዝርዝር ባይሰጡም ዋሽንግተን መሻሻሎች አሉ ብላ ታምናለች ብለዋል።
በዓል ሲመታቸውን ከመፈጸማቸው ወይም ከፈጸሙ በኋላ ከፑቲን ጋር ንግግር አድርገው እንደሆነ የተጠየቁት ትራምፕ "አናግሬዋለሁ፤ አናግሬዋለሁ እንበል። ብዙ ንግግሮች እናደርጋለን ብዬ አጠብቃለሁ፤ ጦርነቱን ማስቆም አለብን" ብለዋል።
"ካወራን ስለምን እንዳወራን አልነግራችሁም" ብለዋል ትራምፕ።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ፑቲና ትራምፕ መነጋገራቸውን ማረጋገጥም ሆነ ማስተባበል እንደማይፈልጉ እሁድ እለት የናገሩትን በዛሬው እለትም ደግመውታል።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ በፑቲንና በትራምፕ ንግግር መካከል የተለያዩ መልእክቶች እየወጡ መሆናቸውንና እሳቸው እያንዳንዱን ነገር እንደሚያውቁ ገልጸዋል።
"ስለዚህ ጉዳይ ሁሉንም ላረጋጋግጥ ወይም ላስተባብል አልችልም" ብለዋል።
ይሁን እንጁ መሪዎቹ የዩክሬኑ ጦርነት በሚቅምበት ጉዳይ ተገናኝተው ለመምከር ዝግጁ መሆናቸውን በተጋጋሚ ሲገልጹ ተደምጠዋል። ሩሲያ የሁለቱ መሪዎች በአሳኡዲ ወይም በአረብ ኢምሬትስ ሊገናኙ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ፑቲን ከሁለት ሳምንት በኋላ ሶስት አመት የሚሞላውን ጦርነት የሩሲያ ህልውና ጉዳይ አድርጠው ይቆጥሩታል። ዩክሬንና ምዕራባውያን አጋሮቿ ደግሞ የቅኝ ግዛት አይነት የመሬት ነጠቃ አድርገው ይመለከቱታል።