ትራምፕና ዘሌንስኪ ከጦፈ ክርክር በኋላ ያለ ስምምነት ተለያዩ
ትራምፕ ዘለንስኪን “በሚሊየኖች ህይወትና በ3ኛ የዓለም ጦርት ቁማር እየተጫወትክ ነው” ብለዋል

ትራምፕ ዘለንስኪን “አሜሪካን አላከበርክም" ሲሉ፤ ዘለንስኪ ዋይት ኃውስን ጥለው ወጥተዋል
የአሜሪካው ፕሬዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ በዋይት ኃውስ ያደረጉት ውይይት ያለ ምንም ስምምነት ተጠናቋል።
ዘለንስኪ ወደ ዋይት ኃውስ ያቀኑት በውድ ማእድናት ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ስምምት ለመፈራረም ቢሆን፤ ሁለቱ ወደ ክርክር እና የቃላት ግጭት አምርቶ ያለ ምንም ሰምምት ተጠናቋል።
ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ጋር የጦፈ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው ውይይታው የተቋረጠው።
በዋየት ኃውስ በኦቫል ፅህፈት ቤት በነበራው ቆይታ ዶናድ ትራምፕ ቮሊድሚር ዜልኒስኪን “አክብሮት የጎደለው ባህሪ” ከሰዋል።
በንግግራው ወቅትም ትራምፕ ዘሌንስኪን “በሚሊየኖች ህይወትና በ3ኛ የዓለም ጦርት ቁማር እየተጫወትክ ነው” ብለዋል።
ዘለንስኪ የሰለም ስምምነት ለመፈረም ዋስትና ያስፈልገናል ቢሉም፤ ትራምፕ "ለመደራደሪያ የሚሆን አቅም እና ሥልጣን የለህም" በማለት አቋርጠዋቸው ያለህ አማራጭ ስምምነቱን መፈረም ነው ካልሆነ አሜሪካ ከዚህ ትወጣለች” ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ዘለንስኪ በሰላም ውይይቱ ዙሪያ ካለመግባባታቸውም ባሻገር "ለሰላም ስትዘጋጅ ተመለሰህ ና" ብለዋል።
ይህንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ዋይት ሀውስን ጥለው የወጡ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ሊያደርጉት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫም ተሰርዟል፡፡