አሜሪካ እና ፊሊፒንስ በአይነቱ ግዙፍ ነው የተባለ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሊያካሂዱ ነው
ልምምዱ በደቡብ ቻይና ባህር አከባቢ የሚደረግ እንደመሆኑ ያለውን ውጥረት እንዳባብስ ተሰግቷል
በልምምዱ ከሁለቱም ሀገራት የተውጣጡ 17 ሺህ ወታደሮች ተሳታፊ ይሆንሉ ተብሏል
አሜሪካ እና ፊሊፒንስ በመጪው ሚያዝያ በአይነቱ ግዙፍ ነው የተባለለትን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሊያካሂዱ ነው፡፡
ልምምዱ ዛምባልስ እና ፓላዋንን ጨምሮ ደቡብ ቻይናን በሚያዋስኑ አምስት ግዛቶች ላይ እንደሚካሄድም ሮይተርስ ዘገቧል፡፡
- አሜሪካ የስለላ ድሮኗ በሩሲያ ጄቶች ተመቶ በጥቁር ባህር መከስከሱን ገለጸች
- አውስትራሊያ ከአሜሪካ የምትገዛቸው የጦር መርከቦች የፓስፊክን የሃይል ሚዛን ይለውጡት ይሆን?
እናም ሀገራቱ ልምምዱን የሚያደርጉት በደቡብ ቻይና ባህር አከባቢ እንደመሆኑ ከቻይና ጋር ያለውን ውጥረት እንዳያባብሰው ተሰግቷል፡፡
በተለይም አንዱ ማሰልጠኛ ማእከል ሚገኘው ለታይዋን ቅርብ በሆነ ስፍራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፊሊፒንስ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮ/ል ሚካኤል ሎጊኮ ፤ ማኒላ እና ዋሽንግተን በሚያደርጉት የጋራ ልምምድ ከሁለቱም ሀገራት የተውጣጡ 17 ሺህ ወታደሮች ተሳታፊ ይሆንሉ ብለዋል፡፡ 12ሺዎቹ የአሜሪካ ወታደሮች መሆናቸውን በመግለጽ፡፡
ልምምዶቹ የባህር እና የባህር ዳርቻዎች ደህንነት ለማረጋገጥ አልመው የሚደረጉ እንደሆነም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡
የጋራ ልምምዱ በቻይና ላይ ያነጣጠረ አይደለም ያሉት ሎጊኮ፤ ነገር ግን "የምናሰለጥነው የሚቃጣብን አደጋ ለመመከት ዝግጁ መሆናችንን ለማሳየት ነው" ብለዋል።
"ማንኛውም ሀገር በግዛቱ ውስጥ የመሰልጠን ፍጹም እና የማይገሰስ መብት አለው... ግዛታችንን የመከላከል ፍጹም እና የማይገሰስ መብት አለን" ሲሉም አክለዋል ቃል አቀባዩ ሎጊኮ፡፡
አሜሪካ እና ፊሊፒንስ በከባድ የጦር መሳሪያውችንም ጭምር የሚታጀበውን ግዙፉ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያው ይሆናል ተብሏል፡፡