ፖለቲካ
ለዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በሚል ወደ አዲስ አበባ የሚመጣ አፍሪካዊ መሪ የለም
ኢትዮጵያ ፕ/ር ሂሩት ወልደማርያምን ለህብረቱ የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ኮሚሽነርነት እጩ አድርጋ ማቅረቧ ይታወሳል
መሪዎቹ ወደ አዲስ አበባ የማይመጡት ጉባዔው በወረርሽኙ ምክንያት በግንባር የማይካሄድ መሆኑን ተከትሎ ነው
የአፍሪካ መሪዎች ለዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ ጉባኤ በሚል ወደ አዲስ አበባ እንደማይመጡ ተነገረ፡፡
መሪዎቹ ወደ አዲስ አበባ የማይመጡት ጉባዔው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በግንባር የማይካሄድ መሆኑን ተከትሎ ነው፡፡
እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጻ ጉባኤው በበይነ መረብ እንጂ በአካል አይካሄድም፡፡
በመሆኑም በጉባኤው ለመሳተፍ በሚል ወደ አዲስ አበባ የሚመጣ አፍሪካዊ መሪ አይኖርም፡፡
ቃል አቀባዩ የሚኒስቴሩን ሳምንታዊ ተግባራት በተመለከተ መግለጫን እየሰጡ ነው፡፡
የዘንድሮው የህብረቱ አመታዊ ጉባኤ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ነው ለ34ኛ ጊዜ የሚካሄደው፡፡
“ጥበብ፣ ባህል እና ቅርስ ልንገነባ ለምንሻት አፍሪካ” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድም ህብረቱ አስታውቋል፡፡
ጉባዔው የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማትን ጨምሮ ሌሎች የሌሎች ኮሚሽነሮች እና ዳይሬክተሮች ምርጫ የሚካሄድበት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ፕ/ር ሂሩት ወልደማርያምን ለህብረቱ የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ኮሚሽነርነት እጩ አድርጋ ማቅረቧ የሚታወስ ነው፡፡