የብሪታኒያዋ ሊዝ ትረስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይመረጣሉ የሚል ግምት አገኙ
ቦሪስ ጀንሰን የቀረበባቸውን ቅሌት ተከትሎ ነበር ከስልጣን እንደሚለቁ ያስታወቁት
ሊዝ ትረስ የቀድሞውን የብሪታኒያ ፋይናንስ ሚኒስትር ሪሹ ሱናክን በማሸነፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸዋል
የብሪታኒያዋ ሊዝ ትሩስ የብሪታኒያው የወግ አጥባቂ ገዥ ፓርቲ እና የሚቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትር መሪ ሆነው ይመረጣሉ የሚል ግምት አግኝተዋል፡፡
ብሪታኒያ በአሀኑ ወቅት በከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣ የኢንዲስትሪ አለመረጋጋት እና የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ውስጥ እንደምትገኝ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ለሁለት ሳምንንታት የቆየው በንዴትና በፓርቲ መሪዎች መካከል ክፍፍል ያስተናገደው ውድድር ትረስ በቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ጋር እንድታጋጭ አድርጓታል፡፡
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለወራት የቆየውን አሉባልታ ተከትሎ ነበር ስልጣን እንደሚለቁ ያስታወቁት፡፡
አሸናፊ የሚሆነው እጩ ወደ ስኮትላንድ በመሄድ ንግስቲቱን ያገኛል፡፡
ትረስ ከተሾሙ ከ2015 ምርጫ በኋላ የኮንሰርቫቲቭስ አራተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ። በዚያ ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱ ከቀውስ ወደ ቀውስ ስትሸጋገር የቆየች ሲሆን በሐምሌ ወር 10.1 በመቶ በሆነው የዋጋ ግሽበት ሳቢያ የረዥም የኢኮኖሚ ውድቀት ነው ተብሎ የሚገመተው።
የ47 ዓመቷ የጆንሰን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትረስ የብሪታንያ የኑሮ ውድነት ችግርን ለመቅረፍ በፍጥነት እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገብተዋል፡፡
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የሃይል ሂሳቦችን ለመቅረፍ እና የወደፊት የነዳጅ አቅርቦቶችን ለማስገኘት እቅድ እንደሚያቀርቡ ትረስ ተናግረዋል፡፡
ትረስ በአመራር ዘመቻዋ ወቅት የግብር ጭማሪን በመሰረዝ እና አንዳንድ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች የዋጋ ንረትን ያባብሳሉ ያሉትን ሌሎች ቀረጥ በመቀነስ ኮንቬንሽኑን እንደምትቃወም ተናግራለች።