ከዓለም በእርዝመቱ 5ኛ የሆነውን ህንጻ ለመውጣት የሞከረ ግለሰብ በፖሊስ ታሰረ
የደቡብ ኮሪያውን ህንጻ ያለመወጣጫ ገመድ ለመውጣት የሞከረ ግለሰብ በፖሊስ ታሰሯል
የደቡብ ኮሪያ ፖሊስ ግለሰቡ 123 ፎቅ ያለውን የሎቲ ዎርልድ ታወር ከማሽ በላይ ከወጣ በኋላ እንዲያቆም አድርጎታል
ከአለም አምስተኛ የሆነውን የደቡብ ኮሪያ ህንጻ ያለመወጣጫ ገመድ ለመውጣት የሞከረ ግለሰብ በፖሊስ ታሰሯል።
የደቡብ ኮሪያ ፖሊስ ግለሰቡ 123 ፎቅ ያለውን የሎቲ ዎርልድ ታወር ከማሽ በላይ ከወጣ በኋላ እንዲያቆም አድርጎታል።
ይህ የ24 አመት እድሜ ያለው እንግሊዛዊ፣ ፖሊስ እና የአደጋ ሰራተኞች እስከሚደርሱ ድረስ አጭር ልብስ ለብሶ ህንጻውን እየወጣ ነበር።
ፖሊስ በጥገና መሰላሉ ወደ ህንጻው ከማስገባቱ በፊት 73ኛ ፎቅ ላይ ደርሶ ነበር።
ሮይተርስ ፖሊስ ስለጉዳዩ ወዲያውኑ አስተያየት አለመስጠቱን ገልጿል።
ቾሱን ኢቦ የተባለው ጋዜጣ የመውጣት ሙከራ ያደረገው ግለሰብ ጆርጅ ኪንግ ቶምኘሰን እንደሚባል ይፋ አድርጓል።
የእንግሊዝ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ይህ ግለሰብ በፈረንጆቹ 2019 ለንደን ውስጥ ህንጻን በመውጣቱ ታስሮ ነበር።
በፈረንዶቹ 2018፣ ፈረንሳያዊው አለን ሮበርት ሎቶ ወርልድ ታወርን ግማሽ ድረስ ከወጣው በኋላ መታሰሩ ይታወሳል።