ማቸስተር ዩናትድ ከተጫወታቸው 6 የፕሪምየርሊግ ጨዋታዎች በሶስቱ ሽንፈት አስተናግዷል
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው በቶትንሀም ተሸነፈ
የሰሜን ለንደኑ ቶትንሀም በኦልድትራፎርድ ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ0 ማሸነፍ ችሏል የቶትንሀም የማሸነፊያ ጎሎችን ጆንሰን፣ ኩሉቬንስኪ እና ሶላንኬ አስቆጥረዋል
የማንችስተር ዩናይትድ አምበል እና የጨዋታ አቀጣጣይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ42ኛው ደቂቅ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል
የተረጋጋ አቋም ማሳየት የተሳነው ማንችስተር በውጤት ቀውስ ውስጥ ይገኛል። ይህን ተከትሎም ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ በከፍተኛ ጫና ውስጥ ይገኛሉ፡፡
በ2024/25 የዝውውር መስኮት ንቁ ተሳትፎ ሲያደርግ የነበረው ቡድኑ በተከላካይ፣ በአማካይ እና አጥቂ ስፍራዎች የሚጫወቱ ተጫዋቾችን 182.5 ሚሊየን ፓውንድ በማውጣት ቢያስፈርምም የአቋም መዋዠቁን ሊቀርፍ አልቻለም፡፡
ባሳለፍነው አመት በሊጉ 8ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ዩናይትድ ዘንድሮ የተሻለ አቋም እንደሚያሳይ ቢጠበቅም ካደረጋቸው 2 ጨዋታዎች ሁለቱን አሸነፎ ፣ አንድ አቻ እና 3 ሽንፈቶችን በማስተናገድ በደረጃ ሰንጠረዡ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ትናነት በተደረጉ ጨዋታዎች አርሰናል ሌስተር ሲቲን 4ለ2 እንዲሁም ቼልሲ ብራይተንን በተመሳሳይ 4ለ2 ማሸነፍ ችለዋል።
በዚህም አርሰናል በ14 ፣ ቼልሲ በ13 ነጥብ በሊጉ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስን 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ የቻለው ኤቨርተን የውድድር አመቱ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል።
በተጨማሪም ፉልሀም ኖቲንገሀምን 1ለ0 ሲያሸንፍ ብሬንትፎርድ ከዌስትሀም ዩናይትድ 1ለ1 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።