ፎቶ ማንሳት እና ቪዲዮ መቅረጽን የከለከለው የምሽት መዝናኛ ቤት
እገዳው የተጣለው ደንበኞች በሙዚቃዎች ከመደነስ ይልቅ ጊዜያቸውን ፎቶ በማንሳት እያሳለፉ ነው በሚል ነው

በብሪታንያ የምሽት መዝናኛ ቤቶች ቁጥር በየዓመቱ እየቀነሰ መጥቷል ተብሏል
ፎቶ ማንሳት እና ቪዲዮ መቅረጽን የከለከለው የምሽት መዝናኛ ቤት
አምበር የተሰኘው የብሪታንያው ምሽት መዝናኛ ቤት ደንበኞች ስልክ ይዘው እንዳይመጡ ከልክሏል፡፡
በማንችስተር ከተማ የሚገኘው ይህ የመዝናኛ ቤት ከዚህ በፊት በሰዎች ዳንስ አየተለየ የደስታ ስሜት አሁን በስልኮች ካሜራ ላይት እየተጨናነቀ እና ዲጄዎችን እና ሌሎች ባለሙያዎች እየተማረሩ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
መዝናኛ ቤቱ ደንበኞቹ የእጅ ስልካቸውን ይዘው እንዳይመጡ የከለከለው ሰዎች በሙዚቃዎች ከመዝናናት ይልቅ ፎቶ በመነሳት እና ቪዲዮ በመቅረጽ ጊዜያቸውን እያሳለፉ ነው በሚል እንደሆነ ቢቢሲ ዘግል፡፡፡
ማስጠንቀቂያውን ችላ ብለው ከነ ስልካቸው የሚመጡ ደንበኞች ደግሞ በስልካቸው ካሜራው ላይ ስቲከር እንደሚለጠፍበትም መዝናኛ ቤቱ ገልጿል፡፡
እንደ በርሊን ያሉ ዝነኛ ምሽት ቤቶች ላይ የእጅ ስልክ ይዞ መግባትን የሚከለክል ህግ ያላቸው ሲሆን ከቅርበ ጊዜ ወዲህ ሰዎች ከበሙዚቃዎች ከመዝናናት ይልቅ ፎቶ በመነሳት የሰዎችን ደስታ እየረበሹ ነው ተብሏል፡፡
በብሪታንያ የምሽት ቤቶች ቁጥር እየተመናመነ የመጣ ሲሆን ኮሮና ቫይረስ ትልቁ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
ኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት በብሪታንያ 1 ሺህ 266 የምሽት በት መዝናኛዎች የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ቁጥራቸው ወደ 786 ዝቅ ብሏል፡፡
በርካቶች የምሽት ቤቱን ውሳኔ ደግፈው አስተያየት የሰጡ ሲሆን የተወሰኑ በተለይም ወጣቶች ደግሞ የምሽት ቤቱን እርምጃ ተችተዋል፡፡