ዘለንስኪ እና ሚቶታኪስ ባለፈው ረቡዕ በሰጡት የጋራ መግለጫ በሚሳይል ጥቃቱ የደረሰውን ውድመት መመልከታቸውን ተናግረዋል
ሩሲያ ባስወነጨፈችው ሚሳይል ዘለንስኪን እና የግሪኩን ጠ/ሚ ኢላማ አድርጋ ሊሆን እንደሚችል ባለስልጣኑ ተናገሩ።
ሩሲያ ባስወነጨፈችው ሚሳይል ፕሬዝደንት ዘለንስኪን እና በጉብኝነት ላይ የነበሩትን የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢላማ አድርጋ ሊሆን ይችላል የሚለውን ግምት መተው እንደማይቻል አንድ ከፍተኛ የዩክሬን ባለስልጣን ተናገሩ።
ሩሲያ ባለፈው ረቡዕ ያስወነጨፈችው ሚሳይል በጥቁር ባህሯ ኦደሳ ወደ ወጭ የሚላክ እህል ማከማቻን እየጎበኙ ከነበሩት ዘለንስኪፐ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኪሪያኮስ ሚቶታኪስ ጥቂት መቶ ሜትሮች ርቀት ላይ ወድቋል።
ሩሲያ ይህን አስተያየት አስተባብላለች።
"ከእኛ 500 ሜትር ርቀት ላይ ነው... በፕሬዝደንቴ ወይም በውጭው እንግዳ ላይ ያነጣጠረ አይደለም ማለት አይቻልም" ሲሉ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ አማካሪ የሆኑት ኢሆር ዞቭክቫ ተናግረዋል።
ዘለንስኪ እና ሚቶታኪስ ባለፈው ረቡዕ በሰጡት የጋራ መግለጫ በሚሳይል ጥቃቱ የደረሰውን ውድመት መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በዚህ ጥቃት አምስት ሰዎች መገደላቸውን የዩክሬን ጦር አስታውቋል።
የሩሲያ ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ዲሜትሪ ሜድቬዴቭ እንደተናገሩት ሩሲያ የልኡካን ቡድኖችን ኢላማ አላደረገችም፤ እንዲህ አይነት ጥቃት እንደማትፈጽም ለማንም ግልጽ ነው ብለዋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱ በተፈጸመበት ቀን ባወጣው መግለጫ የሩሲያ ጦር በወደቡ የነበረ የድሮን ማከማቻን ኢለማ ማድረጉን እና ኢላማው ግብ መምታቱን ገልጿል።
ሩሲያ በዩክሬኗ ኦደሳ ወደብ ላይ የምታደርሰው ጥቃት በተለይ ሩሲያ ዩክሬን እህል ወደ ውጭ መላክ ከሚያስችላት በተመድ አማካኝነት ከደረሰው የጥቁር ባህር ስምምነት ከወጣች በኋላ ጨምሯል።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ሁለት አመት ያለፈው ሲሆን ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን በኩል ከተሞችን እና መንደሮችን በመቆጣጠር ይዞታዋን እያሰፋች ነው።