ፖለቲካ
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከውጭ ጊዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይነት መነሳታቸው ተገለፀ
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሁለት ጊዜያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው አገልግለዋል
በአምባሳደር ዲና ምትክ አምባሳደር መለስ አለም መሾማቸው ተሰምቷል
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከኃላፊነት መነሳታቸው ተሰማ።
ለሁለት ጊዜያት የመስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ የነበሩት አምባሳደር ዲና ከሃላፊነት ስለመነሳታቸው በመንግስት በኩል ይፋዊ ማብራሪያ አልተሰጠም፡፡
ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በየሳምንቱ ይሰጡት የነበረው መግለጫ ከተቋረጠ አንድ ወር በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት መግለጫ ሰጥተው ነበር።፡
በአምባሳደር ዲና ምትክ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት መለስ አለም መሾማቸውን አል ዐይን ማርኛ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች ማረጋገጥ ችሏል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቱ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ሞሸማቸውም ተስምቷል።
አምባሳደር ዲና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው።