ሜሲ ይህን ስመጥር ሽልማት ያሸነፈው በውድድሩ የመጨረሻ እጩ ሆነው ከቀረቡት ሃላንድ እና ምባፔ በልቆ በመገኘቱ ነው
ሊዮነል ሜሲ እና ቦንማቲ የፊፋ ምርጥ ተጨዋቾች ሆነው ተመረጡ።
ትናንት ምሽት በተካሄደው የፊፋ የ2023 "ምርጥ" ሽልመት መርሃግብር የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮነል ሜሲን ምርጥ ብሎ መምረጡን ፊፋ በድረገጹ አስታውቋል።
- ክርስቲያኖ ሮናልዶ “ከሜሲ ጋር የነበረን የፉክክር ዘመን አብቅቷል” አለ
- ሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ማያሚን የዋንጫ ባለቤት ለማድረግ መቃረቡን ተከትሎ በምርጫዬ 'ደስተኛ ነኝ' አለ
ከፈረንጆቹ ታህሳስ 20፣2022 እስከ ነሐሴ 20፣2023 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው ምርጥ የወንድ ተጨዋቾች ልየታ የተካሄደው።
ሜሲ በ2022 ያገኘውን የፊፋ ምርጥነት ሽልማት ማስጠበቅ ችሏል።
ፊፋ እንደገለጸው ሜሲ ይህን ስመጥር ሽልማት ያሸነፈው በውድድሩ የመጨረሻ እጩ ሆነው ከቀረቡት ኢርሊኔግ ሃላንድ እና ክሊያን ምባፔ ልቆ በመገኘቱ ነው።
በለንደን በተካሄደው "ዘ ቤስት ፊፋ ፋትቦል አዋሬድስ" ላይ ሜሲ ያስመዘባቸው ስኬቶች ተነስተዋል።
ሜሲ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኖች፣ አምበሎች፣ ባለሙያ ጋዜጠኞች እና በመላው አለም የሚገኙ ደጋፊዎች በተሳተፉበት እና ብርቱ ፉክክር በተካሄደበት ምርጫ አንደኛ ሆኗል።
በኳታር አስተናጋጅነት የተካሄደው የአለም ዋንጫ አሸናፊ ሜሲ እና በኖርዌይው አለምአቀፍ ተጨዋች ሀላንድ መካከል የነበረው ውድድር በእኩል 48 ነጥብ ላይ ቆሞ የነበረ ቢሆንም የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች ለሜሲ የሰጡት የመጀመረያ ጥቆም በመብለጡ ሁለቱን ለመለየት አስችሏል።
ፈረንሳያዊው አጥቂ ምባፔ ደግሞ በ35 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ተሸላሚ መሆን ሆኗል።
በዚሁ የሽልማት ውድድር ላይ የአለም ዋንጫ አሸናፊዋ የ25 አመቷ አይታና ቦንማቲ በሴቶች የፊፋን ምርጥ ተጨዋች ሽልማት አሽንፋለች።
ቦንማቲ ባለፈው ጥቅምት ወር የባሎን ዶር ሽልማትም ማሸነፏ ይታወሳል።
ቦንማቲ ሽልማቶቹን ያገኘችው ባርሴሎናን ለሻምፒዮንስ ሊግ ታይትል እና ሀገሯን ስፔንን ደግሞ ለአለም ዋንጭ ድል ካበቃች በኋላ ነው።