ሚሳዔልና ተተኳሽ ቦምቦችን ጭኖ በሰዓት ከ2 ሺህ ኪ.ሜ በላይ የሚበረው “ሚኮያን ሚግ-35” ጄት
ሚኮያን MIG-35 ሩሲያ ካሏት አደገኛ የጦር ጄቶች ውስጥ አንዱ ነው
እስከ ከ300 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኙ የባሀር ላይና የአየር ላይ ጠላት ኢላማዎችን መለየት ይችላል
ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት ሩሲያ ካሏት ጦር የውጊያ ጄቶች ውስጥ በአደገኛነቱ እና በፈጣንነቱ ብዙ ይነገርለታል።
ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት በፈረንጆቹ 2007 የተመረተ ሲሆን፤ ሩሲያ አሁን ላይ ከዩክሬን ጋር ከገጠመችው ጦርነትን ጨምሮ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ላይ እንተጠቀመችበት ኤር ፎርስ ቴክኖሎጂ ድረ ገጽ አስነብቧል።
ተዋጊ ጄቱ ክሊሞቭ አር ዲ 33 MK የሚል መጠሪያ ያለው ሁለት ሞተሮች የተገጠሙለት ሲሆን፤ ከመሬት ለመነሳት 122 ሜትር የመንደርደሪያ፤ ለማረፍ ደግሞ 137 ሜትር ርዝመት ቦታ ያስፈልገዋል።
በሰዓት ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አየር ላይ የሚከንፈው ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት፤ በአንድ ጊዜ በተሞላለት ነዳጅ ከ3 ሸህ ኪሎ ሜትሮች ባለይ፤ እዛው አየር ላይ ነዳጅ ተከሞላለት ደግሞ ከ5 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ እንደሚችል ታውቋል።
ተዋጊ ጄቱ ፀረ መርከብ እና ፀረ አውሮፕላን ሚሳዔሎችን ጨምሮ የተለያዩ ተተኳሽ ቦምቦችን የመታጠቅ አቅም ያለው እንደሆነ ይነገራል።
ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት ከሚታጠቃቸው እና ከሚያስወነጭፋቸው መሳሪያዎች መካከልም ሚግ-35 Kh-29TE ሚሳኤል እና KAB-500Kr TV ቦምቦች ተጠቃሽ ናቸው።
ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት አየር ክልልን ጦሶ የገባን የጠላት አውሮፕላን ከ160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መለየት እንደሚችልም ኤር ፎርስ ቴክኖሎጂ ድረ ገጽ መረጃ ያመለክታል።
ታዲያ ይህ የጦር ጄት የአየር ክልል ጥሶ የገባን የጠላት አውሮፕላን ሚግ-35 Kh-31P ፀረ-ራዳር ሚሳኤል በመጠቀም የሚያወድም መሆኑ ተነግሯል።
ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት በተጨማሪም የሀገርን የውሃ ክልል ጥሶ የገባን መርከብ ከ300 ኪሎ ሜትር ላይ የመለየት ብቃት ያለው ሲሆን፤ አስፈላጊ ሆኖ ከገተኘ Kh-31A ፀረ-መርከብ ሚሳኤል በማስወንጨፍ መምታት ይችላል ተብሏል።