“ዚርኮን” ከድምፅ በ9 እጥፍ የሚፈጥነው አዲሱ የሩሲያ ሱፐር ሶኒክ ሚሳዔል
ፕሬዝዳንት ፑቲን የሩሲያ መርከቦች በቀጣይ ወራት ውስጥ አዲሱን ሱፐር ሶኒክ ሚሳዔል ይታጠቃሉ ብለዋል
“የማይበገር” የተባለው ሚሳዔሉ ከባህር ላይ ተተኩሶ የአሜሪካዋ ዋሽንግተንን ለመምታት 5 ደቂቃ ይበቃዋል
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ የጦር መርከቦች በቅርብ ዋት ውስጥ “ዚርኮን” የተባለውን አዲስ ሱፐርሶኒክ ሚሳዔል እንደሚታጠቁ አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ በትናትናው እለት እንዳስታወቁት፤ ዚርኮን አዲስ ሱፐርሶኒክ ሚሳዔል “የማይበገር” አዲስ የጦር መሳሪያ ነው።
አዲሱ የሩሲያ ዚርኮን ሱፐርሶኒክ ሚሳዔል ከድምፅ በ9 እጥፍ የሚፈጥ እና በቀላሉ የማይመታ እንደሆነም ነው እየተነገረ ያለው።
ዚርኮን ሱፐርሶኒክ ሚሳዔል ምን የተለያ ያደርገዋል?
ሚሳዔሉ እስከ 1 ሺሀ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የማጥቃት አቅም ያለው ሲሆን፤ ሚሳዔሉ በፍጥነቱ በዓለማችን ላይ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም።
ሩሲያ በሚሳዔሉ ላይ ሙከራ ማድረግ የጀመረችው በፈረንጆቹ 2021 የበልግ ወቅት ሲሆን፤ የመጀመሪያዎቹ ሙከራዎችም ከሰርጓጅ መርከቦች ላይ የተደረገ ነው ተብሏል።
ሚሳዔሉ ለባህር ኃይል እና ለመድር ጦር እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ሲሆን፤ ለባህር ኃይል የተሰራው ለሰርጓጅ እና ባህር ላይ ለሚጓዙ መርከቦችም እንዲታጠቁት ተደርጎ ነው የተሰራው።
የሚሳዔሉ ፍጥነት ከድምጽ በ9 እጥፍ ይበልጣል የተባለ ሲሆን፤ ይህም የአየር መከላከያ ስርዓቶች አስቸጋሪ እና የማይመታ አድርጎታል።
ሚሳዔሉ በአየር ላይ እያለ የመገለባበጥ አቅም ያለው ሲሆን፤ አውዳሚ የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ የኒውክሌር አረር መሸከም የሚችል መሆኑም ተነግሯል።
የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ሚሳዔሉ ከዓለም አቀፍ የውሃ አካል ላይ ከተተኮሰ የአሜሪካዋ ዋሽንግተንን ለመምታት 5 ደቂቃ ብቻ ይፈጅበታል።
የቢሪታኒያው ሚረር ጋዜጣ እንዳስነበበው ከሆነ ደግሞ ሚሳዔሉ ከዓለም አቀፍ የውሃ አካል ላይ ከተተኮሰ የብሪታኒያዋ ለንደን ከተማን ለመምታ 4 ደቂቃ ብቻ ይበቃዋል ተብሏል።
የሩሲያው ታስ የዜና ወኪል መንነታቸው ያልተጠቀሰ የጦረ ምንጭን ጠቅሶ ባወጣው መረጃ፤ ዚርኮን ሱፐርሶኒክ ሚሳዔልን የታጠቁ የሩሲያ የጦር መርከቦች በቀጣይ መስከረም ወር ወደ ስምሪት እንደሚገቡ አስታውቋል።