የሩሲያ እና የኔቶ ወታደራዊ አቅም ሲነጻጸር ምን ይመስላል?
ፕሬዝደንት ፑቲን በተደጋጋሚ የሚያሰሟቸው ዛቻዎች ሶስተኛው የአለም ጦርነት ሊከሰት ይችላል የሚለውን የምዕራባውያን ስጋት ጨምሮታል
ፕሬዝደንት ፑቲን ኔቶ ጦር ወደ ዩክሬን የሚልክ ከሆነ ሩሲያ ለመግጠም ዝግዱ ናት ሲሉ በቅርቡ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል
የሩሲያ እና የኔቶ ወታደራዊ አቅም ሲነጻጸር ምን ይመስላል?
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን በተደጋጋሚ የሚያሰሟቸው ዛቻዎች ሶስተኛው የአለም ጦርነት ሊከሰት ይችላል የሚለውን የምዕራባውያን ስጋት ጨምሮታል።
ፕሬዝደንት ፑቲን ኔቶ ጦር ወደ ዩክሬን የሚልክ ከሆነ ሩሲያ ለመግጠም ዝግዱ ናት ሲሉ በቅርቡ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
ወደ ሶስተኛው የአለም ጦርነት የሚያመራው ግጭት አይቀሬነት ያመላከቱት ፑቲን "በዛሬ የድል ቀን ስትራቴጂክ ኃይላችን ለመዋጋት ዝግጁ መሆኑን አስምረን መናገር እንፈልጋለን" ሲሉ መናገራቸውን የእንግሊዙ ጋዜጣ ዘሚረር ዘግቧል።
ፑቲን ይህን ያሉት ሩሲያ ድሮን እና ሀይፐርሶኒክ ሚሳይሎችን በመጠቀም በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ውድመት ባደረሰችበት ወቅት ነው።
እንደጋዜጣው ከሆነ ሩሲያ ከደቀነችው ስጋት ጎን 32 አባላት ያሉት የኖርዝ አትላንቲክ ትሪቲ ኦርጋናይዜሽን (ኔቶ) አንድ ትሪሊዮን ወታደራዊ በጀት፣ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ወታደር እና 700ሺ ተጠባባቂ ኃይል አለው።
የሩሲያ እና የኔቶ ጦር ንጽጽር
እግረኛ ወታደር
1.4 ሚሊዮን ወታደር ያላት ሩሲያ በወታራዊ ጥንካሬ ከአለም ሁለተኛ ብትሆንም፣ የኔቶ ወታደር ከ5.8 ሚሊዮን በላይ ሲሆን ይህም የሩሲያን አምስቱ እጥፍ ገደማ ይሆናል።
የሩሲያ መደበኛ ወይም አክቲቭ ወታደሮች ቁጥር 858,000 ሲሆን የኔቶ ደግሞ ሶስት ሚሊዮን ነው።
የሩሲያ ተጠባባቂ ኃይል ብዛት 250ሺ ሲሆን የኔቶ ደግሞ 1,720,000 ነው።
አየር ኃይል
የኔቶ የአየር ኃይል ጠቅላላ 20,633 ኤርክራፍት የታጠቀ ሲሆን የሩሲያ በብዙ ቁጥር አንሶ 4,182 ነው።
ሩሲያ 773 ተዋጊ ጄቶች የታጠቀች ሲሆን ኔቶ ደግሞ 3398 ጄቶች አሉት። ለመሬት ውጊያ የሚውል ጄት ወይም ግራውንድ አታክ ኤርክራፍት ሩሲያ ኔቶ ካለው 1108 ጋር ሲነጻጸር 744 ታጥቃለች።
በኔቶ እና ሩሲያ መካከል ያለው ሄሊኮፕተር ብዛት ልዩነት እየሰፋ መጥቷል። ኮምባት ሄሊኮተርን በተመለከተ ሩሲያ 537 የታጠቀች ሲሆን ኔቶ ደግሞ 1439 ሄሊክተሮችን የታጠቀ ነው።
የምድር ኃይል
ለውጊያ የሚሆኑ ዋና የውጊያ የታንኮች ብዛት ሩሲያ ብለጫ ወስዳለች። ሩሲያ 12,566 ታንኮች ያሏት ሲሆን ኔቶ ደግሞ 12,408 ታንኮችን ታጥቋል። ሩሲያ 151,641 ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ያሏት ሲሆን የኔቶ ደግሞ ወደ አንድ ሚሊዮን ይጠጋል።
ሩሲያ ራሱ በሚተኩስ ወይም ሰልፍ ፕሮፔልድ ከባድ መሳሪያ ብልጫ አላት። የሩሲያ 6575 ሲሆን የኔቶ ደግሞ 4532 ነው። የታወር አርቲለሪ ወይም የታወር ከባድ መሳሪያ ቁጥር በሩሲያ 4336 ሲሆን በኔቶ ደግሞ 6554 ነው።
ሩሲያ ያላት ጠቅላላ የጦር መርከብ 598 ሲሆን ኔቶ 12 ዲስትሮየርን ጨምሮ 2151 የጦር መርከቦችን ታጥቋል።
ኤየርክራፍት ኬሪየር(የጦር አውሮፕላኖች ማረፊያ መርከብ)
ሩሲያ ምንም የአየርክራፍት ኬሪየር የላትም። ኔቶ በአንጻሩ 13 አየርክራፍት ኬሪየር አለው።
ባህር ሰርጓጅ መርከብ
ሩሲያ 70 ባህር ሰርጓጅ ውይም ሰብማሪን ያላት ሲሆን ኔቶ 143 አለው። ሩሲያ 59 የቅኝት ጀልባዎችን የታጠቀች ሲሆን 259 ጀልባዎች የተጣቀው ኔቶ በብዙ ቁጥር ይበልጣል።
የፈንጅ ማምከኛ
ሩሲያ 49 የፈንጅ ማምከኛ ወይማ ማስወገጃ ሲኖራት ኔቶ በ151 በመታጠቅ ብለጫ ወስዷል።
የኑክሌር ጦር መሳሪያ
በኑክሌር የጦር መሳሪያ ብዛት ሩሲያ የኔቶ ሀገራትን ትበልጣለች። 5977 የኑክሌር ዋርሄድ ወይም ተተኳሽ የታጠቀችው ሩሲያ 5943 ተተኳሽ የታጠቀውን ኔቶን ትበልጣለች።