የትግራይ ክልል ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ገንዘብ አልደረሰኝም ብሏል
ግብርና ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ በጀት መላኩን ገለጸ
ለትግራይ ክልል የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ በጀት መላን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በዚህም መሰረት በ2013 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ አመት ማለትም ከሀምሌ እስከ መስከረም መጨረሻ 153 ሚሊዮን 612 ሺ 266 ብር ለትግራይ ክልል መላኩን የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በ2013 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ማለትም ከሀምሌ እስከ መስከረም መጨረሻ 153 ሚሊዮን 612 ሺ 266 ብር ለትግራይ ክልል መላኩን የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የትግራይ ክልል ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብና ለጋሽ ሀገሮች ለአርሶ አደሮች በሴፍቲኔት ፕሮግራም ሲሰጥ የቆየው ገንዘብ በፌዴራል መንግስት እንዳልተላከ እና መላክ የነበረበት 285 ሚልዮን ብር እንዳልደረሰው ገልጾ ነበር፡፡
የግብርና ሚኒስቴር በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው በ2012 ዓ.ም እንዲሁም በ 2013 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት ከፌዴራል መንግስት ለትግራይ ክልል ለልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚሆን በጀት ተልኳል ብሏል፡፡
ሚኒስቴሩ “እዉነታን ደብቆ የህዝብን ችግር ለዕድሜ ማራዘሚያነት ከመጠቀም ተባብሮ ሰርቶ የህዝብን ችግር መቅረፍ የህዝብ ወገንተኝነትን ያረጋግጣል” ሲል የክልሉን መንግሥት ነቅፏል፡፡
በ2012 በጀት ዓመት ለትግራይ ክልል ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚሆን 1ቢሊዮን 448,671,541 ብር መላኩን ገልጿል፡፡
በ 2013 የመጀመሪያ አንደኛ ሩብ ዓመት ደግሞ ለሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ ለትግራይ ክልል 153 ሚሊዮን 612 ሺ 266 ብር መላኩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡