የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮናው ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚካሄደው የለንደን ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያ ልምምዱን አድርጓል ተብሏል
ሞ ፋራህ በፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ሰባተኛ ወጣ።
ሞ ፋራህ የጋቦን ፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በ30 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ ሰባተኛ ሆኖ አጠናቋል።
የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነው ሞ ፋራህ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚካሄደው የለንደን ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያ ልምምዱን አድርጓል ተብሏል።
አትሌቱ 2023 ጡረታ ከመውጣቱ በፊት የመጨረሻው የውድድር ዓመቱ እንደሚሆን ባለፈው በጥር ወር አስታውቋል።
ጋቦን ላይ ኬንያዊው ቪንሴንት ኪፕኬሞይ በ28 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ አንደኛ በመውጣት አሸንፏል።
ፋራህ እ.ኤ.አ. በ2022 የለንደን ማራቶን በሽንጥ ጉዳት ምክንያት ያልተሳተፈ ሲሆን፤ የዘንድሮው ውድድር ከ2019 በኋላ የመጀመሪያው ሙሉ ማራቶን ይሆናል ተብሏል።
ለብሪታኒያዊው የመጨረሻ የለንደን ማራቶን ውድድር እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን፤ ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ በታሪክ አምስት ፈጣን የማራቶን ሯጮች መካከል ከአራቱ ጋር አንገት ለአንገት ይያያዛል።