ፖለቲካ
የመሃመድ ቢን ዛይድ የነገ የአንካራ ጉብኝት…ለምን?
ዩኤኢ እና ቱርክ እንደወትሮው ያልሆነውን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማለስለስ የበለጠ የማጠናከር ፍላጎት አላቸው
የአቡዳቢው ልዑል ነገ ቱርክን ሊጎበኙ እንደሆነ ተነግሯል
የአቡዳቢ ልዑል አልጋወራሽ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ጦር ምክትል ጠቅላይ አዛዥ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ነገ ቱርክን ሊጎበኙ ነው፡፡
ቢን ዛይድ በፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኦርዶጋን ግብዣ ነው አንካራን የሚጎበኙት፡፡
በጉብኝቱ በጋራ የሁለትዮሽ እና የትብብር በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ጭምር እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
ኦርዶጋን ባሳለፍነው ነሃሴ ወር መገባደጃ ላይ ከቢን ዛይድ ጋር የስልክ ቆይታ አድርገው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
“ቱርክ በአስፈላጊ ሰዓት ያሳየችውን ወዳጅነት አደንቃለሁ”-ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
ይህ የዩኤኢ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ አል ናህያን አንካራን ከጎበኙ ጥቂት ሳምንታት በኋላ የሆነ ነው፡፡
የዩኤኢ መሪዎች ሪፐብሊክ ሆና የተመሰረተችበትን ብሔራዊ በዓል በቅርቡ ላከበረችው ቱርክ የእንኳን ደስ አላችሁ የመልካም ምኞች መግለጫ መልዕክት ልከው እንደነበርም አይዘነጋም፡