“ዩኤኢ ከሃገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ማጥበቋን ትቀጥላለች”- ልዑል አልጋወራሽ መሃመድ ቢን ዛይድ
መሪዎቹ በተገኙበት ዘርፈ ብዙ ስምምነቶች ተፈርመዋል
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ብሪታንያ ያቀኑት ልዑል አልጋወራሹ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጋር ተገናኝተዋል
የአቡዳቢው ልዑል አልጋወራሽና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ዩኤኢ) ምክትል የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ዛሬ ብሪታንያ ለንደን ገብተዋል፡፡
ቢን ዛይድ ለንደን ሲደርሱ በዳውኒንግ ጎዳና በሚገኘው ቤተ መንግስት በብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንስን ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸውም ነው የተገለጸው፡፡
የዩኤኢው ሞሃመድ ቢን ዛይድ ፈረንሳይ ፓሪስ ገብተዋል
መሪዎቹ በሁለቱም ሀገራት ስታራቴጂካዊ ትብብር እና የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ትኩረት አድርገው ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
የቢን ዛይድ ጉብኝት የሁለቱም ሀገራት ባለስልጣናት በተለያዩ ወቅቶች ያደረጓቸውን ጉብኝቶች ተከትሎ የተደረገና በሁለቱም ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው፡፡
ዩኤኢ እንደፈረንጆቹ 1971 ከተመሰረተች ወዲህ ብሪታንያ የዩኤኢ የበርካታ ዓመታት ወዳጅና ትልቅ ዋጋ ያላት ሀገር ሆና እየቀጠለች መሆኗንም ነው ከዩኤኢ የውጭ ጉዳይ መስርያ ቤት ድረ-ገጽ የተገኘው መረጃ የሚያመላክተው፡፡
ዩኤኢ እና ብሪታንያ ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ እና ባህል ትስስራቸውን ለማጠናከር የሚያስችል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራትም ናቸው፡፡
የብሪታንያ ብሄራዊ ስታቲስቲክስ በፈረንጆቹ ጥቅምት 31፣2014 ያወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው እንደፈረንጆቹ በ2013 የሀገራቱ የንግድ ልውውጥ መጠን 12 ነጥብ 36 ቢሊዮን ፓውንድ (72 ቢልዮን ድርሃም) ደርሶ ነበር፡፡
የ12 ቢሊዮን ፓውንድ የንግድ መጠኑ በሀገራቱ ስምምነት መሰረት ለ2015 ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በሁለት ዓመታት ቀድሞ ሊሳካ ችሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዩኤኢ እና ለእስራኤል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
የሀገራቱ የንግድ ልውውጥ መጠኑ እንደ ኢነርጂ፣ ፋይናንስ፣ አቬሽን፣መከላከያ እና አገልግሎት በመሳሳሰሉ ሌሎች ዘርፎችም በክፍተኛ ሁኔት አድገዋል፡፡
እንደፈረንጆቹ በ2011 የተቋቋመው የዩኤኢ-ብሪታኒያ የንግድ ም/ቤት የንግድ ልውውጥ እቅድ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሳካ ትልቅ ሚና እንደተጫወተም ይነሳል፡፡
የንግድ ም/ቤቱ ዋና ተልእኮ ንግድና ኢንቨስትመንት ማሳደግ፣ የብሪታንያ ኩባንያዎች በዩኤኢ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ማበረታታትና ማገዝ እንዲሁም በተመሳሳይ የዩኤኢ ኩባንያዎች በብሪታንያ እንዲሰማሩ ማድረግ እና የተሻሉ የገበያ እድሎች ማጤን ነው፡፡