ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በአሜሪካ የመጀመሪያውን ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን ሊያደርጉ ነው
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን የፊታችን ሰኞ ይጀምራሉ
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይፋዊ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ተነግሯል
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን በአሜሪካ የመጀመሪያቸው የሆነውን ይፋው የስራ ጉብኝት ሊያደር ነው።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በአሜሪካ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት የፊታችን ሰኞ መስከረም 12 እንደሚጀምሩም ከአረብ ኢምሬትስ የዜና አገልግሎት ዋም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣን ከያዙ በኋላ በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብንት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው እንደሆነም ተነግሯል።
ፕሬዝዳንቱ በአሜሪካ ነጩ ቤተ መንግስት ዋይት ኃውስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይፋዊ አቀባበል እንደሚደረግላቸውም ተነግሯል።
ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በአሜሪካ ቆይታቸውም ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር እንዲሁም ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።
ከዋነኛ የውይይት አጀንዳዎቻው ውስጥም ከ50 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የአሜሪካ እና የአረብ ኢምሬትስ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚያተኩር ተነግሯል።
በተለይም በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክሎጂ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀነስ እና የህዋ ምርምር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ እና በታዳሽ ኃይል ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ እና ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በዓለም አቀፋዊ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም የሚጠበቅ ሲሆን፤ የጋዛው ጦርነት እና የሱዳን ጦርነትን በውይይታቸው ከሚነሱ ጉዳዮች መካከል ናቸው።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከሁለት ዓመት በመካለኛው ምስራቅ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ጋር ተገናኝተው መምከራቸው ይታወሳል።
ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር ባደረጉት ውይይትም ከአረብ ኢሬትስ ጋር ያለውን ግንኙነት በሚጠናከርበት ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል።