የአረብ ሀገራትን እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ በጋራ እርመጃ መውሰድ አስፈላጊነት ላይ ተስማምተዋል
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በግብፅ ይፋዊ የስራ ጉብኘት አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ኤል አሚን ከተማ የሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ ተቀብለዋቸዋል።
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በግብፅ ቆይታቸው ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ ጋር በሁለትዮሽ እና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ የትብብር አቅጣጫዎች እና የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚያስችሉ በርካታ ተስፋ ሰጭ ዕድሎች ላይ መክረዋል።
በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ እና የግብጹ አቻቸው አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ሰነዶች እንዲኁም በአህጉራዊ እና አለምአቀፍ መድረኮች ላይ ባሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
በዚህም የአለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ አለመግባባቶችን እና ቀውሶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የውይይት እና የዲፕሎማሲ ዘዴዎችን በመጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
የአረብ ሀገራትን እያጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥየአረብ ሀገራትን አንድነት መመለስ እና በጋራ እርመጃ መውሰድ አስፈላጊነት ላይ ተስማምተዋል።