ኢኮኖሚ
ዩኤኢ ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጎብኝታለች
በኮሮና ምክንያት የዓለም ቱሪዝም በተጎዳበት በዚህ ወቅት ከጥር እስከ ጥቅምት ባሉት 10 ወራት ውስጥ ከ4 ሚሊዮን የሚልቁ ጎብኚዎችን አስተናግዳለች
በጥቅምት ወር ውስጥ ብቻ 1 ሚሊዮን ጎብኚዎች ዩኤኢን ጎብኝተዋል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጎብኝታለች፡፡
ዩኤኢከጥር እስከ ጥቅምት 2021 ዓመት ውስጥ ባሉት 10 ወራት ውስጥ 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ጎብኚዎች መጎብኘቷን የአገሪቱ ቱሪዝም እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ ዩኤኢን እንደሚጎበኙ አስታወቁ
የዓለም ቱሪዝም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ክፉኛ በተጎዳበት በዚህ ወቅት የተባበሩት አረብ ኤምሬት የጎብኚዎችን ትኩረት ስባለች፡፡
ዩኤኢ የሳምንቱን የእረፍት ቀናት ወደ ቅዳሜ እና እሁድ ቀየረች
በዩኤኢ ከተሞች የሚገኙ ሆቴሎች እና ሞቴሎች 9 ነጥብ 4 ሚሊዮን የመኝታ ክፍሎችን የሸጡ ሲሆን የህ አሃዝ በ2019 ዓመት የተሸጡ መቆያ ክፍሎች 7 ሚሊዮን ብቻ ነበር፡፡
በዚህ ዓመት በጥቅምት ወር ውስጥ ብቻ 1 ሚሊዮን ጎብኚዎች ወደ ዩኤኢ አቅንተው አገሪቱን የጎበኙ ሲሆን አሃዙ በፈረንጆቹ 2020 ዓመት የጎብኚዎች ቁጥር ጋር የማይነጻጸር መሆኑም ተገልጿል፡፡
ዩኤኢ ይህን ያክል መጠን ባለው ጎብኚዎች መጎብኘቷ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለተጎዳው የዓለማችን ቱሪዝም ተስፋ ነውም ተብሏል፡፡