ዩኤኢ ከመጪው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ አርብ እና ቅዳሜ የሳምንቱ የእረፍት ቀናት እንደማይሆኑ አስታውቃለች
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) የሳምንቱን የእረፍት ቀናት ወደ ቅዳሜ እሁድ ልትቀይር ነው፡፡
ዩኤኢ ከመጪው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ የሳምንቱ የእረፍት ቀናት አርብ እና ቅዳሜ መሆናቸው ቀርቶ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሆኑ መወሰኑን የሃገሪቱ ዜና አገልግሎት (ዋም) አስታውቋል፡፡
በውሳኔው መሰረት ከአርብ ከሰዓት መልስ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ የእረፍት ቀናት ይሆናሉም ተብሏል፡፡
በባህረ ሰላጤው ሃገራት አርብ እና ቅዳሜን ማረፍ የተለመደ ነው፡፡
የዩኤኢ የደህንነት አማካሪ በኢራን ጉብኝት አካሄዱ
ኤምሬት ግን ይህን ልምድ ለመቀየር ወስናለች፡፡ በአዲሱ ውሳኔ መሰረትም የሳምንቱ የስራ ቀናት አራት ቀናት ከስድስት ሰዓታት ብቻ ነው የሚሆኑት፡፡
ውሳኔው ምርታማነትን ለማሳደግ እና የተጣጣመ የስራ ህይወትን ለመጠበቅ በማሰብ የተላለፈ መሆኑን የሃገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡
ዩኤኢ 80 ራፋል ተዋጊ የጦር ጄቶችን ከፈረንሳይ ልትገዛ ነው
በፈረንጆቹ ከመጪው ጥር 1/2022 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናልም ተብሏል፡፡
ውሳኔው በሁሉም የመንግስት ተቋማት እንደሚተገበርም ተገልጿል፡፡
የአቡ ዳቢ እና የዱባይ መንግስታት ውሳኔውን ተቀብለው ተግባራዊ ለማድረግ መወሰናቸውንም አስታውቀዋል፡፡