ከአራት ሽህ በላይ ዶክተሮች ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት መነጠሏን ተከትሎ የጤና አገልግሎቶችን ለቀው መውጣታቸው ተነገረ
ማደንዘዣ፣ የሕፃናት ሀኪም፣ የልብ የቀዶ ሀኪም እና የስነ አእምሮ ሀኪሞች ለቀው ከወጡት ከፍተኛውን ቁጥር ይዘዋል ተብሏል
ብሬግዚት እየተባለ የሚጠራው የብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣት የሀገሪቱን የዶክተሮች እጥረት እያባባሰ መሆኑተነግሯል
ከአራት ሽህ በላይ የአውሮፓ ሀኪሞች ከዩናይትድ ኪንግደም ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ጋር ላለመስራት መወሰናቸው ታውቋል።
ይህም ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት ከተነጠለች በኋላ የሀገሪቱን የዶክተሮች እጥረት እያባባሰ መሆኑን የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ማመላከታቸው ተነግሯል።
ከአውሮፓ ህብረት እና ከአውሮፓ ነፃ የንግድ ማህበር ሀገራት ብሪታኒያ ከመውጣቷ በፊት የህክምና ባለሞያዎች በሰፊው ይቀጠሩ ነበር ተብሏል።
ከብሬግዚት በፊት ከፍተኛ የሰራተኞች ብዛት ነበሯቸው የተባሉ የማደንዘዣ ባለሙያ፣ የህፃናት ህክምና፣ የልብና የደም ቀዶ ጥገና ህክምና እና የአዕምሮ ህክምናን ጨምሮ አራት ልዩ ልዩ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚመለመሉና በጤና ተቋማት እንደሚያገለግሉ ኑፊልድ ትረስ የተባለ ተቋም ባሳተመው ጥናት ይፋ አድርጓል።
በፈረንጆቹ 2021 በአጠቃላይ 37 ሽህ 35 የአውሮፓ ዶክተሮች በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እየሰሩ ነበር። አሀዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ይህም ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት ባትወጣ ኖሮ ከተገመተው 41 ሽህ በላይ ያነሰ ሆኖ ተገኝቷል። ጥናቱን የጠቀሰው የአናዶሉ ዘገባ የህክምና ባለሞያዎቹ ቁጥር ከታቀደው በአራት ሽህ 285 ያነሰ ነው።
"ግኝቶቹ እንደሚያመለክቱት በልዩ ባለሙያዎች ዘርፍ የአውሮፓ ዶክተሮች ቁጥር መቀዛቀዝ አሳውይቷል። የዩናይትድ ኪንግደም ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ባለሞያዎቹን ለመተካት ብቃት ያላቸው ሰራተኞችን ማግኘት መቸገሩ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የህክምና እጥረቶችን አባብሶታል" ሲል ጥናቱ ገልጿል።
"በስደቱ ገፊ ምክንያቶችን ለማወቅ ጠለቅ ያለ ጥናት ማድረግ ቢያስፈልግም እ.ኤ.አ. በ2016 ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት የተወሰነው ውሳኔ ሚና የሚጫወተው ይመስላል" ብሏል ጥናቱ።