በሶማሊያ ከ700 በላይ ህጻናት በስነ-ምግብ ማእከላት ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ
የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ ያልተሳካ የዝናብ ወቅት አጋጥሞታል
በፈረንጆቹ 2011 በሶማሊያ በተከሰተው ረሃብ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ህይወት የቀጠፈ ሲሆን አብዛኞቹ ህጻናት ነበሩ
በመጪዎቹ ወራት የሶማሊያ አንዳንድ ክፍሎች በረሃብ ሊጠቁ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት ኤጀንሲ (ዩኒሴፍ)አስታውቋል፡፡
የዩኒሴፍ የሶማሊያ ተወካይ ዋፋ ሰኢድ "በዚህ አመት ከጥር እስከ ሀምሌ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 730 የሚሆኑ ህጻናት በምግብ እና ስነ-ምግብ ማዕከላት” መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ ያልተሳካ የዝናብ ወቅት አጋጥሞታል፡፡
በፈረንጆቹ 2011 በሶማሊያ በተከሰተው ረሃብ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ህይወት የቀጠፈ ሲሆን አብዛኞቹ ህጻናት ነበሩ።
የዩኒሴፍ የሶማሊያ ተወካይ ዋፋ ሰኢድ በጄኔቫ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "በዚህ አመት ከጥር እስከ ሀምሌ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ማዕከሎች 730 የሚሆኑ ህጻናት” መሞታቸው ተዘግቧል
“ነገር ግን የብዙዎች ሞት ሪፖርት ስለማደረግ ቁጥሩ የበለጠ ሊሆን ይችላል" ብለዋልዋፋ ሰኢድ፡፡
ማዕከላቱ ከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ላለባቸው ህጻናት እንዲሁም እንደ ኩፍኝ፣ ኮሌራ ወይም ወባ ያሉ ሌሎች ችግሮች ያሉባቸው ሲሆን በመላ አገሪቱ ያለውን ሁኔታ እንደ ቅጽበተ-ፎቶ ተቆጥረዋል።
"የችግሩ ግዝፈት ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም፡፡ በሞቃዲሾ የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ ቪክቶር ቺንያማ ብዙዎች ልጆቻቸውን በመንገድ ላይ (ወደ ማእከል) የሞቱ ቤተሰቦችን አግኝቻለሁ”ሲሉ ዋፍ ሰኢድ ተናግረዋል።
ዩኒሴፍ እንደገለጸው በህጻናት ላይ የበሽታ ወረርሽኝ እየጨመረ ሲሆን በቅርብ ወራት ውስጥ 13ሺ የሚሆኑ የኩፍኝ ተጠርጣሪዎች ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 78 በመቶው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው፡፡